



ዶ/ር መላኩ ታዬ የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስትና የስኳር ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ነው። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማከም፣ በማስተማርና በምርምር በማገልገል ላይ ይገኛል። በተጨማሪም በተለያዩ የጤና ዘርፎች ንቁ የመሪነት ተግባራት ያከናውናል። የስኳር ህመምና ተያያዥ በሽታዎችን ለመቋቋም የሚያስችል ጠንካራ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ለመፍጠር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል። በተረጋገጠ ሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ የጤና መረጃ ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ የጤና ምክሮችን በዘርፈ ብዙ መንገዶችና የሚዲያ አማራጮች ያስተምራል።
የዶ/ር መላኩ የስፔሻሊቲ ህክምና ትኩረት ዘርፎች
የስኳር ህክምና
የውፍረት ህክምና
የኮሌስትሮል ህክምና
ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ
የእንቅርት ህክምና
የአጥንት መሳሳት ህክምና፣ የቫይታሚን ዲ እጥረት ህክምና
ሌሎች የሆርሞን መዛባት ህመሞች ህክምና