የአሜሪካ የጤና ድጋፎች መቋረጥ ስጋቶችና እድሎች
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣን እንደተቆናጠጡ ከፈረሟቸው ፕሬዝዳንታዊ አዋጆች መካከል ጤናን የሚመለከቱ ስር ነቀል ፖሊሲዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ሆነዋል። አወዛጋቢ የጤና ሚኒስቴር ከመሾም እስከ አሜሪካን ከአለም ጤና ድርጅት (WHO) ማስወጣት፤ ቁልፍ የጤና ተቋማትን ኮሚኒኬሽን ከመዝጋት እስከ የተቋማትን አካታችነት፣ እኩልነት እና ፍትሃዊነትን ለማስፈን የወጣ ፕሮግራም ማገድ ሰፊ ክርክር አስነስተዋል። ትራምፕ በመጀመሪያው የነጩ ቤተ መንግስት ጊዜያቸው…