Dr. Melaku Taye

Diabetes remission – የስኳር ህመምን ማዳፈን ወይስ ማዳን?

የዛሬዉን ሃተታ በአንድ የታካሚዬ ታሪክ ልጀምር። ጋሽ ተስፋዬ የ50 አመት ጎልማሳ ናቸው። የዓይነት 2 የስኳር ህመም ህክምና ከጀመሩ ከአሥር ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። በየቀኑ ኢንሱሊን ይወጋሉ፤ የስኳር ኪኒንም ይወስዳሉ። ታዲያ አንድ ቀን የሚወዱት ወዳጃቸው  á‰´áˆŒáŒáˆŤáˆ ላይ አንድ ቪዲዮ ላከላቸው። ቪዲዮው እንዲህ ይላል፦ «ሐኪሞች የማይነግሯችሁ ምሥጢር! ስኳር በ90 ቀን ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይድናል። መድሃኒትህን ተውና ይህችን ምስጢራዊ…

የኢትዮጵያ ፍልስፍናዊ እሴቶች

ከኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በስተቀር ሌላው አለም አዲስ አመት የሚቆጥረው ከጃንዋሪ ወር ጀምሮ ነው። የአሮጌው አመት መጨረሻ ሰባት ቀናት በአፍሪካዊ አሜሪካዊያን ዘንድ ክዋንዛ (Kwanzaa) ተብሎ ይከበራል። ይህም የፓን አፍሪካ ሰባት ፍልስፍናዊ እሴቶች ለማዘከር ታስቦ የሚውል ነው። በመከባበር፣ በመተሳሰብ እና በመትጋት ለጋራ ዓላማ እንዴት አብሮና ተዳምሮ መኖር እንደሚቻል የሚያስትምሩ ሰባት ማህበረሰባዊ የአፍሪካ እሴቶች ናቸው። ኢትዮጵያም ምድረ ቀደምት…

የማረጥ (menopause) ምልክቶች

ማረጥ ኖርማል የሴትነት ህይወት ተፈጥሯዊ ምእራፍ ነው። እንቁላል አመንጭ የሆኑት የሴት አካል (እንቁልጢ / ኦቫሪ) ሾል መጨረስን ያሳያል። ማረጥ በራሱ በሽታ አይደለም። ነገር ግን አንዳንድ ሴቶች ምቾት የሚነሱ ምልክቶቹ ሊያስተናግዱ ይችላሉ። በተለይም አንዳንዶቹ በእንቅልፍ፣ ስሜት፣ ጾታዊ ግንኙነት፣ ማህበራዊ ግንኙነቶች እና በስራ ላይ ተጽእኖ ማሳደር የሚደርሱ ምልክቶች ሊያዩ ይችላሉ። እንዲህ ሲሆኑ ተገቢ የህክምና እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል።…

የእርጣት ትኩሳት (Menopausal Hot Flashes)

ማረጥ ተፈጥሯዊ የሴትነት ህይወት ምእራፍ እንጅ በሽታ አይደለም። ነገር ግን ብዙ ሴቶች ምቾት የሚነሱ የማረጥ ምልክቶች ሊያስተናግዱ ይችላሉ። የተለምደው እና በጣም የሚረብሸው የማረጥ ምልክት የሰውነት ሙቀት ሙቀት ማለት ነው። በተለይም ደረት አካባቢ የሚነሳ የሚዘፍቅ ማተኮስ እና ሌሊት ላይ ማላብ ይገኝበታል። በሳይንሳዊ አጠራሩ vasomotor symptoms (VMS) ይባላል። እነዚህ የማተኮስ እና የማላብ ስሜቶች ድንገት ብልጭ የሚሉ ክስተቶች…

እርጣት (menopause)

ማረጥ የሴቶች ሆርሞን ኡደት አንዱ ምዕራፍ ነው። እርጣት የሚባለው የሴት የወር አበባ በቋሚነት የሚቆምበት ጊዜ ነው። ይህ የሚሆነው ኦቫሪ እንቁላልን ማምረት ማቆም ተከትሎ የሴት ሆርሞኖች (ኢስትሮጅን፣ ፕሮጀስትሮን) ስለሚቀንሱ ነው። የወር አበባ ሙሉ በሙሉ ከመቆሙ በፊት የሚቆራረጥበት የሽግግር ወራት/አመታት ሊኖሩት ይችላሉ። በአብዛኛው ከ45 እስከ 55 አመት እድሜ ላይ ይመጣል። የወር አበባ በእርግዝና፣ በህመም፣ በእርግዝና መከላከያ መድሃኒት…

“ቆሽቴ አረረ” ስንል?

ኢትዮጵያዊያን ሲናደዱ፣ ሲጨነቁ፣ በንዴት ድብን ሲሉ ‘ቆሽቴ አረረ’ ይላሉ። በእርግጥ ይህ አገላለጽ  áˆáŠ• ትርጉም አለው? ይህ ንግግር ሾለ ስኳር ህመም መነሻ ምክንያት ያመላክታል። ምንም እንኳን ሰዎች ስለሕክምና የአስኳላ ትምህርት ባይኖራቸው ስለበሽታ አመጣጥ ያላቸውን ጥንታዊ ፍልስፍናዊ አረዳድ ይዳስሳል። ስንቆጣ ‘ኧረ ቆሽቴ አረረ፣ አቃጥለህ ልትገድለኝ እኮ ነው‘ ስንል፤ በሃይል ስንበሳጭ ቆሽት ላይ ምን ጉዳት እንደሚፈጠር እና ከስኳር…

ስግጥና ወይስ ፕሮፌሽናሊዝም – ማን ይፈምሳል?

የሰው ልጅን ቀልብ መግዛት አዲሱ ገበያ እየሆነ ነው። የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች የሚጠቀሙት ዋናው ማጥመጃ ስሜታችንን ነው። የሰው ልጅ ሳይኮሎጂ የገባቸው ናቸው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አሸናፊዎች። የሚያወዛግብ፣ የሚያስፈራ፣ የሚያስቆጣ፣ የሚያነሳሳ፣ የሚያስቅ አሊያም የሚያስደንቅ ድንቃድንቅ ዜና በመርጨት ተከታታዮቻቸውን ያጠምዳሉ። ከባድ ሳይኮሎጂ ነው የሚጫወቱት። የማህበራዊ ሚዲያ ቫይራል አልጎሪዝም ቫይራል የመውጣት አልጎሪዝም አስማት አይደለም። በጥበብ የሚመጣ ነው። በፈጠራ…

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብሄራዊ አገልግሎት – ግዴታ ወይስ ውዴታ?

ኢትዮጵያ ሚሊኒየሙን ከተቀበለች ከጥቂት አመታት በኋላ የሞቀ ቤቴን ትቼ እውቀት ለመገብዬት ዩኒቨርሲቲ ስገባ ከቤተሰብ ጫንቃ ወርጄ ወደ ‘ራስን የመቻል’ ጉዞ የጀመርኩ መስሎኝ ነበር። የሆነው ግን ቦታ ከመቀየር ውጭ እንደእናት ባይሆንም ሌላ ኮምፎርት ዞን ነበር። የትምህርት ክፍያ የለ፣ የቤት ኪራይ አላውቅ፣ የመብራት አይሉኝ! ምግብ አላበስል፣ አስቤዛ አላስብ! ከእንቅልፍ የሚያነቃ ሃሳብ አልነበረብኝም። አንዲት ስራዬ እንደምንም ክላስ መግባትና…

Dhukkuba Vaayirasii Maarbarg (Marburg Virus Disease)

Vaayirasiin Maarbarg dhukkuba daddarbaa, ho’a qaamaa qabuudha.Gosa vaayirasii  Filoovaayirasii jedhamuun kan ramadamu yoo ta’u, vaayirasii Iboolaa waliin walitti dhufeenya guddaa qaba. Sadaasa 5, 2018 sababni weerara dhukkuba ho’aa dhiiga dhangalaasu Vaayirasiin Dhufu  kan Itoophiyaa keessatti namoota tokko tokko miidhe vaayirasii Maarbarg ta’uun mirkanaa’eera. Barreeffamni barsiisaa kun maalummaa, daddarbiinsa, mallattoolee, yaala, fi ittisa vaayirasii Maarbarg irratti xiyyeeffata….

የማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus Disease)

የማርበርግ ቫይረስ ተላላፊ የሆነ የንዳድ በሽታ ነው። ዝርያውም ፊሎቫይረስ በመባል የሚመደብ ሲሆን ከኢቦላ ቫይረስ ጋር ይቀራረባል። ዛሬ ህዳር 5፣ 2018 ዓም በኢትዮጵያ የተወሰኑ ሰዎችን ያጠቃ በቫይረስ የሚመጣ አደገኛ ትኩሳት ወምፍሳስ ደም (Viral Hemorrhagic Fever) ወረርሽኝ መንስኤው የማርበርግ ቫይረስ መሆኑን አረጋግጧል። ይህ ትምህርታዊ ጽሁፍ ስለማርበርግ ቫይረስ ምንነት፣ ሥርጭት ፣ ምልክቶች ፣ ህክምና እና የመከላከል መንገዶች ዙሪያ…

Scroll to Top