Dr. Melaku Taye

በቫይረስ የሚመጣ አደገኛ ትኩሳት ወምፍሳስ ደም (Viral Hemorrhagic Fevers)

ደም መፍሰስ ሊያስከትል የሚችሉ የቫይረስ ኢንፌክሽኖች የአር ኤን ኤ ቫይረስ ዝርያ ያለቸው ከባድ ሕመሞች ናቸው። በዋነኝነት የሚተላለፉት በአስተላላፊ ትንኞች ወይም በበሽታው በተያዙ ሰዎች የሰውነት ፈሳሽ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ነው። የበሽታው ዋና ምልክቶች ከፍተኛ ትኩሳት እና ደም መፍሰስ ያካትታል። ህክምናው በአብዛኛው የሚያካትተው የሰውነት ፈሳሽ በግሉኮስ መተካት፣ በባለሙያ ክትትል ማድረግ እና ተጓዳኝ ችግሮችን ማከም ላይ ያተኩራል። ጥብቅ…

ጤናዬን እጠብቃለሁ፣ በፈጣሪም አምናለሁ

አንዳንድ ሰዎች ዘመናዊ ህክምና መጠቀም (ለምሳሌ ክትባት) በእምነታቸው ላይ የሚሰነዘር ጥቃት አድርገው ሲያዩት ተመልክቻለሁ። ህክምና መፈለግ የእምነት መጓደል አድርገው የሚቆጥሩም አይጠፉም። ለመሆኑ የሚያድን መድሃኒት ወይም ክትባት መኖር የጸሎታችን መልስ ማግኘት አይደለምን?  ፈጣሪ የሰጠንን ጥበብ በመጠቀም የፈጣሪን ፈዋሽነት ማመን መገለጫ መንገድ አይደለምን?   በዚህ ጽሁፍ ሃይማኖተኛ ሰዎች እምነታቸው ሳይቀነስ ዘመናዊ ሕክምናን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ለማሳየት እሞክራለሁ። ሃይማኖት…

ጤናማ የተመጣጠነ ማእድ

ለስኳር፣ ውፍረት ወይም ኮሌስትሮል ህክምና የሚመጡ ታካሚዎች ስለአመጋገባቸው የሚያጋሩኝ ታሪኮች ከሞላ ጎደል ተመሳሳይነት አላቸው። ስለአመጋገብ ልማዳቸው ስጠይቃቸው ‘ኧረ እንዲያው ጥሎብኝ እንጅ ስኳር ከየት አግኝቼ አብዝቼ?’ በሚል ብስጭት የሚመልሱልኝም አሉ። እንደምንም ተረጋግተው ሲዘረዝሩት ግን ‘ለቁርስ ግማሽ ፍርፍር በግማሽ እንጀራና አንድ መለስተኛ የገብስ ዳቦ ብቻ ነው የምበላው‘  ይጀምሩና ‘ረፋድ ላይ ለቡና ቁርስ መዳፍ የምታክል ቂጣ ከቆሎ ጋር…

የእግር ጉዞ ማዘውተር ጤናን ያለመልማል

አዘውትሮ መራመድ ከተቻለ መሮጥ ለተሻለ ጤና ጉልህ ሚና ይጫወታል። እርምጃ ለአካላዊና አእምሯዊ ጤናን እንደሚፈውስ የተረጋገጠ ለሁላችን የተሰጠን ጸጋ ነው። በዚህ ጽሁፍ በእግር መጓዝ የሚሰጠንን የጤና በረከቶች እንዳስሳለን። እየተራመድን! አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልማድ እንዲሆንብን ማድረግ ይገባል። እኔ በበኩሌ ወክ ማድረግ አብሶ መሮጥ ሱስ ሆኖብኛል ብል ማጋነን አይሆንም። ሲደክመኝ መሮጥ ነው የማስበው፤ ስራ ጫና ሲበዛ ራመድ ራመድ…

ኤች ዲ ኤል (high-density lipoprotein, HDL)

በአንድ ወቅት ለአንድ ታካሚ የኮሌስትሮል መድሃኒት እንዲዎስድ ከብዙ ሰአት ውይይት (‘ኧረ እባክህ ለልጆችህ ስትል’ ልመና) በኋላ ተስማምተን የኮሌስትሮል መቀነሻ መድሃኒት ማዘዣ ጽፌ በቀጠሮ ለመገናኘት ተለያዬን። ከሁለት ወር በኋላ ሲመለስ ስለ ‘የኮሌስትሮል የጤና ጥቅሞች’ የሚወሸክቱ የማህበራዊ ሚዲያ ቪዲዮዎችን አሰባስቦ ይዞ መጣ። መረጃ መሰብሰብ ያለ ነው። ነገር ግን የኮሌስትሮል መቀነሻ መድሃኒት በማዘዝ ‘እነዚህን የኮሌስትሮል ጥቅሞች’ ላስቀርበት እንደነበር…

ኮሌስትሮል ለጤና ጎጂ ነውን?

በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ ጤና ነክ ‘አሉሽ አሉሽ ወሬዎች’ መካከል ‘ኮሌስትሮል የጤና ጉዳት አያመጣም እንዲያዉም ሊጠቅም ይችላል’ የሚል አሳች መረጃ ይገኝበታል። ‘ደግሞስ እንደኢትዮጵያ ያለ ገና በቀን ሶስቴ መብላት እውን ላልሆነበት ሃገር፣ ጮማ ሳንቆርጥ? ቅቤ ሳንጠጣ? የምን ኮሌስትሮል ነው?!’ የሚሉም አይጠፉም። ይህ አስተሳሰብ የኮሌስትሮል ችግርን ጮማ የሚያዘወትሩ፣ ውፍረት የሚያጠቃቸው የአደጉ ሃገሮች በሽታ ብቻ አድርጎ የመቁጠር የተሳሳተ ግንዛቤ…

ስኳር ህመም ጋር የሚመጣ የኮሌስትሮል መዛባት (Diabetic Dyslipidemia)

ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለምከታተላቸው የስኳር ታካሚዎች የኮሌስትሮል መድሃኒት ሳዝዝ ከሚያጋጥሙኝ የታካሚዎች ምላሽ መካከል አንዱና ዋነኛው ‘ዶክተር፣ እኔ አልደላኝ፣ ጮማ አልቆርጥ፣ ቅቤ አልጠቀም፣ ያማረ አልበላ። እንዴት ነው እኔ ኮሌስትሮል የሚኖርብኝ? ኑሮን ሳላሸንፍ ኮሌስትሮል ከየት ይመጣል? ለምንድን ነው እንደሃብታም የኮሌስትሮል መድሃኒት የምወስደው? ደሞ ሰራተኛ የለኝ በየት እርፌ ስለፋ እኮ ነው የምወለው!’ የሚል ይገኝበታል። ይህ አስተሳሰብ የኮሌስትሮል ችግርን…

የስቴሮይድ መድሃኒቶችን ካለአግባብ ለህመም ማስታገሻነት መጠቀም ጉዳቶች (Inappropriate glucocorticoid use)

ካለጤና ባለሙያ ትእዛዝ የስቴሮይድ መድሃኒቶችን (Glucocorticoids) ለህመም ማስታገሻነት በተደጋጋሚ መጠቀም አደገኛ የጤና ችግሮች ያስከትላል። ብዙ ሰው እነዚህን በሃኪም ማዘዣ ብቻ መታዘዝ ያለባቸውን መድሃኒቶች ከየፋርማሲው ለማንኛውም ህመም ማስታገሻነት እየገዛ በየወሩ ወይም አልፎ አልፎ መርፌ መወጋት የተለመደ ሆኗል። በጣም የተለመደው Diclo-Dexa (diclofenac + dexamethasone) አደባልቆ መወጋት ነው። ለሪህ፣ ለጀርባ ህመም ወይም ሌላ ህመም ለማስታገስ ሃይለኛ ነው ስለሚባል…

በኮሌስትሮል መድሃኒቶች ዙሪያ የሚነዙ ሃሰተኛ መረጃዎች (statin misinformation)

‘ዶክተር፣ እኔ የኮሌስትሮል መድሃኒት መውሰድ አቁሜያለሁ። ቲክቶክ ላይ እንዳየሁት ከሆነ ስታቲን መውሰድ ለጤና ጎጂ ነው። ጉበቴን ነክቶታል፣ እግሬን ሸምቆኛል፣ ሲጀመር እኔ ጮማ አልበላ ኮሌስትሮል የለብኝም።’ ያለኝ ከጥቂት ወራት በፊት ከድንገተኛ ልብ ድካም (heart attack) በስንት መድሃኒት ድጋፍ የተረፈ አንድ ታካሚ ነው። እንደብዙዎች ሁሉ ያልተረጋገጠ፣ ምንጩ የማይታዎቅ የማህበራዊ ሚዲያ አሳች መረጃ በመስማት እንዲህ ጤናን አደጋ ላይ…

የኤምፖክስ (mpox) በሽታ የቆዳ ሽፍታ

የኤምፖክስ በሽታ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው። የበሽታው ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት አንድ ሰው ለቫይረሱ ከተጋለጠ ከሳምንት በኋላ ሲሆን አንዳንዴ በቶሎ ወይም ሌላ ጊዜ ዘግየት ብሎ ሊጀምር ይችላሉ። የኤምፖክስ ምልክቶችን ለመጥቀስ ያክል ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ራስ ምታት፣ የመገጣጠሚያ ህመምና ድካም ፣ ጉንፋን መሰል ምልክቶች ይገኙበታል። ቆዳ ላይ የሚወጣ ቁስል / ሽፍታ የኤምፖክስ በሽታ ዋነኛው…

Scroll to Top