‘ዶክተር፣ እኔ የኮሌስትሮል መድሃኒት መውሰድ አቁሜያለሁ። ቲክቶክ ላይ እንዳየሁት ከሆነ ስታቲን መውሰድ ለጤና ጎጂ ነው። ጉበቴን ነክቶታል፣ እግሬን ሸምቆኛል፣ ሲጀመር እኔ ጮማ አልበላ ኮሌስትሮል የለብኝም።’ ያለኝ ከጥቂት ወራት በፊት ከድንገተኛ ልብ ድካም (heart attack) በስንት መድሃኒት ድጋፍ የተረፈ አንድ ታካሚ ነው። እንደብዙዎች ሁሉ ያልተረጋገጠ፣ ምንጩ የማይታዎቅ የማህበራዊ ሚዲያ አሳች መረጃ በመስማት እንዲህ ጤናን አደጋ ላይ የሚጥል ወሳኔ ሊወስን ችሏል። አንዳለመታደል ሆኖ የልብ ድካሙ ድጋሜ ቢመጣ ህይወቱን ሊያሳጣው የሚችል ከመጀመሪያ የባሰ ነው የሚሆነው።
ከክትባት ቀጥሎ ከፍተኛ ሃሰተኛ የጤና መረጃዎች ከሚሰራጩባቸው መድሃኒቶች መካከል ቀዳሚው የኮሌስትሮል መድሃኒት የሆኑት ስታቲኖች (statin) ነው። በቀላሉ ‘ስታቲን’ የሚለውን ቃል ጎግል ላይ ስናስስ የሚመጡልን የአልጎሪዝም አማራጮች የስታቲንን መርዛማነት፣ የዶክተሮች ሴራ፣ ጥቅም የሌለው ወዘተ የመሳሰሉ አሉታዊ አሳች ውሸቶች ይበዛሉ። በመጀመሪያዎቹ የጎግል ገጽ ላይ የሚመጡት አብዛኛዎቹ ድህረ ገጾች የስታቲንን የጤና ጥቅሞች በመካድ ሃሰተኛ መረጃዎችን የሚነዙ ናቸው። ጭራሽ ኮሌስትሮል ከፍ ሲል ነው ለጤና ጥሩ የሚሆነው ብለው የሚቀደዱ ‘የሳይንስ ከሃዲዎችም’ አይጠፉም። እንዲህ አይነት ሳይንሳዊ እውቀት በሌላቸው ወይም ባለሙያ ሆነው አለማወቅ የጋረዳቸው ሃኪም-ጠቀስ ከፊል-ሳይንሳማ ግለሰቦች የሚጋሩ ኢ-ሳይንሳዊ የኢንተርኔት መረጃዎች ብዙዎችን የዋሆች ያስታሉ። በዚህም ምክንያት ተዘናግተው የስታቲን መድሃኒት አልወስድም የሚሉ ወይም የሚያቋርጡ ሰዎች ላልተፈለገ የልብ ህመም ይጋለጣሉ።
የሚደንቀው ግን የስታቲን መድሃኒቶችን ጥቅም የሚክዱ ሲያሻቸውን ስለስታቲኖች ጉዳት በመዘብዘብ ፍርሃት የሚነዙ ሰዎች ድብቅ አጀንዳ ዘመናዊዉን ህክምና በማጣጣል የባህል ህክምናና ቫይታሚኖችን ለመሸጥ የሚደልሉና በከፍተኛ ገንዘብ የሚሸቅሉ ማስታዎቂያ ሰሪዎች መሆናቸው ነው። በጥቃቅን መጽሄቶች፣ ጋዜጦችና ማህበራዊ ሚዲያ ‘ኮሌስትሮል የልብ ህመም መንስኤ አይደለም፤ ስታቲን አይጠቅምም፤ እንዲያዉም የኮሌስትሮል መብዛት ለጤና ጠቃሚ ነው ስለዚህ ቅቤህን ጠጣ፣ ጮማህን ቁረጥ ….’ እያሉ የተረጋገጠ እውነትን የሚቃወሙ ያፈረሱ ሊቃውንት-ነን ባዮች በየጊዜው ብቅ እያሉ የሚረብሹ ነበሩ፣ አሁንም አሉ፣ ወደፊትም አይጠፉም። ብዙውን ጊዜ የባህል ህክምና የሚያሻሽጡ፣ የምግብ ኢንደስትሪ የሚያስተዋውቁ፣ ‘በአቋራጭ የቦርጭ ማጥፊያ 30 መንገዶች’ መጻፋቸውን የሚቸበችቡ፤ በሳይንስ ያኮረፉ፣ ህክምና የተቀየሙ፣ ከዩኒቨርሲቲ የተባረሩ አሊያም የመቃወም አባዜ እና የመጠራጠር ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ናቸው።
የስታቲን ተቃዋሚዎች ክርክር እንደአንዳንድ አክራሪ ሃይማኖተኞች ነው። ለመስማት የሚቀሉ ቋንቋዎችን በመጠቀም ጥርጣሬ ይነዛሉ፣ ፍርሃት ያነግሳሉ። የተሳሳተ አመለካከታቸውን ለማረም በፍጹም ዝግጁነት የላቸውም። ከእነዚህ ሰዎች ጋር ለማስረዳት መከራከር ከንቱ ጉንጭ ማልፋት ነው። ተመክረውም፣ ተምረውም ስለማይቀየሩ የእኔ መልስ ‘ሞኝ የተከለውን ብልህ አይነቅለውም’ና ከነድንቁርናችሁ ኑራችሁ ሙቱ ብዬ ላሽ ነው የምላቸው።
እንደሚታወቀው የልብ እና ተያያዥ የደም ስር ህመሞች (cardiovascular disease) የአለማችን ቁጥር አንድ ገዳይ በሽታ ነው። ለዚህ የልብና የደም ስር ህመም ዋነኛው አጋላጭ መንስኤ ደግሞ በደም ውስጥ ከፍ ያለ ኮሌስትሮል መሆኑ ለበርካታ አስርት አመታት የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ጎጂ ኮሌስትሮል በደም ስር ግርድግዳ ላይ እንደማስቲካ እየተጣበቀ የደም ስር እንዲደርቅና እንዲጠብ በማድረግ የደም ፍሰትን ሂደት ያውካል። በሂደት የደም ቧንቧዎች መደፈን ያስከትላል። ይህ የደም ስር መጥበብ ልብ ላይ ሲከሰት ድንገተኛ የልብ ድካም (Heart attack) የሚባል ገዳይ የሆነ ከባድ ድንገተኛ አደጋ ይደርሳል። ወደ አንጎላችን የሚሄደው የደም ስር ሲጎዳ ደግሞ ድንገተኛ የአንጎል መታዎክ (ስትሮክ) ይባላል። ወደእግር የሚሄደው የደም ፍሰት ሲቋረጥ (peripheral arterial disease) ደግሞ ጋንግሪን (gangrene) ያመጣል። እነዚህ የደም ስር ህመሞች ሁሉም መንስኤቸውና ህክምናቸው ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን በአንድ ላይ ስር የሰደደ የደም ስር ህመም (atherosclerotic cardiovascular diseases, ASCVD) ተብለው ይጠራሉ።
ኮሌስትሮል የእነዚህ የደም ስር ህመሞች ዋነኛ መንስኤ መሆኑ ከተረጋገጠ ግማሽ ክፍለ ዘመን አልፎታል። እንደስታቲን ያሉ የኮሌስትሮል መቀነሻ መድሃኒቶች የልብ እና ተያያዥ የደም ስር በሽታዎችን በእጅጉ እንደሚቀንሱም በበርካታ ጥናቶች የተረጋገጠ እውነት ነው።
ስታቲን (statin) – ዋና የኮሌስትሮል መቀነሻ መድሃኒት
ስታቲን የልብና የደም ስር ሀመሞች ህክምና የጀርባ አጥንት ናቸው። የልብ ህመምን እንዲሁም ሌሎች የደም ስር ህመሞችን ተጋላጭነት በእጅጉ የሚቀንሱ፣ ዉጤታማ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንደሆነ በበርካታ ጥናቶች እና ምርምሮች የተረጋገጠ ነው። ስታቲኖች ጎጂ ኮሌስትሮልን ከመቀነስ ባለፈ በበርካታ መንገዶች የደም ስር ጤናን ይጠብቃሉ። የልብ ድካምንን እና ሌሎችንም ስር የሰደዱ የደም ስር ህመሞች ከ25 እስከ 40 በመቶ ያህል ይቀንሳሉ። ስለሆነም የልብ ህመም ላለባቸው ወይም ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው (ለምሳሌ ስኳር ህመም፣ የደም ግፊት፣ በዘር የሚመጣ የኮሌስትሮል ችግር ወዘተ) ሰዎች ይታዘዛሉ።
የስታቲን መድሃኒቶችን ውጤታማነት እና ደህንነት የሚያረጋግጡ በርካታ ሳይንሳዊ ማስረጃዎች አሉ። የስታቲን ጥናታዊ ጽሁፎችን በአንድ ቦታ የሚከትበው the Cholesterol Treatment Trialist Collaboration የተባለውን የባለሙያዎች የምርምር ቡድን የሚያወጣቸውን ጥናቶች ብቻ ማንበብ ስለስታቲን ያለን ማንኛዉም ጥርጣሬ ለማጥራት በቂ ነው።
ስታቲኖች አደገኛ የጎኞሽ ጉዳት ያመጣሉ የሚለው የተሳሳተ መረጃ ይሰማል። እውነታው ግን ስታቲን መድሃኒቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ ሲሆን የከፋ የጎንዮሽ ጉዳት የማምጣት እድላቸው እምብዛም ነው። በስታቲን ምክንያት የሚከሰቱት አንዳንድ መጠነኛ የጎንዮሽ ጉዳት ቢከሰት እንኳ በቀላሉ ሊታከሙ የሚችሉ ናቸው።
ይልቁንም የስታቲን የጤና ጥቅሞች ሊያመጡ ከሚችሉት ጉዳት በእጅጉ ይበልጣል። የልብና የደም ስር ጤናን በመጠበቅ የማይተካ ሚና ይጫወታሉ። ስታቲኖች እንኳን ከፍተኛ ኮሌስትሮል ላለባቸው ሰዎች መጠነኛ ኮሌስትሮል መጠን ላላቸው እንኳን የልብ ህመምን በመቀነስ ያለእድሜ መሞትን ይከላከላሉ።
ስለሆነም የልብ ድካም ሳይከሰትብን ወይም ስትሮክ ሳይመታን በጊዜ ከሃኪም ጋር በመመካከር እንዳስፈላጊነቱ ስታቲን መጠቀም ይሻላል።
ስለስታቲን ለታካሚዎች እንዴት ብናስረዳ ይሻላል?
ስታቲን ወሳኝ መድሃኒት ሆኖ ሳለ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት ብዙዎች ጋር ሳይደርስ ከቀረ ከንቱ ልፋት ነው የሚሆነው። የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ዘንድ የግድ መድረስ አለበት። ይህን ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች ከታካሚ ጋር ጊዜ ሰጥቶ በማስረዳትና ጥርጣሬዎችን በማስረጃ በማስተማር የስታቲኖችን ቅቡልነት ማረጋገጥ ይቻላል።
በመጀመሪያ ስለስታቲኖች ታካሚው የሚያስበውን ማናቸውም ሃሳቦች ማዳመጥ ይገባል። ስለስታቲን የሚያውቁትን፣ የሰሙትን መረጃዎች መጠየቅ ታካሚው ስላለው ግንዛቤ ለመረዳት ይረዳል። የተሳሳተ ሳይንሳዊ ያልሆነ አመለካከትና መረጃ ካለ ማረቅ ይገባል። ይህን ስናደርግ ግን የታካሚውን ስጋቶች ማጣጣል ሳይሆን ማስረዳት ነው የሚገባው። ርህራሄ የተሞላ ለታካሚው የትምህርት ደረጃ የሚመጥን ሳይንሳዊ መረጃ በማካፈል አብዛኛዎቹ ጥርጣሬዎች ይጠራሉ።
አንዱ የተሳሳቱ መረጃዎች መነሻ የኮሌስትሮል መብዛት የራሱ የሆነ የህመም ምልክት እንደሌለው ሁሉ ስታቲን መድሃኒት ሲጀመር ወዲያዉኑ የሚሻሻል የጤና ምልክት የለም። ስለሆነም ስታቲን መጀመሬ ምንም አይነት ፈጣን ለውጥ አላመጣም ሊያስብል ይችላል። መድሃኒቱን ሳቆመውም ወዲያዉኑ የመጣብኝ ችግር የለም ሊሉ ይችላሉ። ይህን ለማስተካከል የስታቲኖችን አሰራርና የጤና ቱሩፋቶች በስፋት ማስረዳት ይገባል። የስታቲን መድሃኒቶች ጥቅም እንደህመም ማስታገሻ የአጭር ጊዜ እፎይታ ሳይሆን የረጅም ጊዜ ጥቅም ነው ያላቸው። ስታቲኖች ወደፊት ሊመጣ የሚችልን የልብ ድካም ወይም ስትሮክ አስቀድሞ መከላከል ወይም አንዴ ከመጣ ድጋሜ እንዳይከሰት የደም ስር ጤናን መጠበቅ ነው ስራቸው።
ለምሳሌ ራስ ህመም ሲሰማን የህመም ማስታገሻ ፓራሲታሞል/ፓናዶል ስንወስድ ወዲያዉኑ ህመሙ ይታገሳል። መድሃኒቱ ሲያልቅም ህመሙ ቶሎ ይመለሳል። ስታቲኖች አሰራራቸው እንዲህ አይደለም። ስታቲን ስንወስድ ወዲያዉኑ የሚታይ ፈውስ ላይሰማን ይችላል። ስታቲን መውሰድ ስናቆምም ወዲያዉኑ የሚመጣ ችግር አይታየንም። ስታቲን በመውሰድ የምናገኘው የጤና ጥቅምም ሆነ በማቆማችን የሚከሰቱ መዘዞች ከወራትና ከአመታት በኋላ ነው የሚታዩት።
ስታቲን መድሃኒት ስራዉን ሲሰራ እንደመኪና ላይ የደህንነት ቀበቶ ነው። ሁሌም መኪና ስንነዳ ወይም ስንሳፈር የደህንነት የመቀመጫ ቀበቶ ማሰር ይገባል አይደል? ይህን የምናደርገው መንገዱ ሳይመች ሲቀር፣ ስንደነቃቀፍ ወይም ገደል አፋፍ ስንደርስ ብቻ አይደለም፤ ሁሌም ቀበቶ ማሰር ግድ ነው። እጋጫለሁ በሚል ፍርሃት ሳይሆን ከስንት አንዴም ቢሆን ድንገት አደጋ ቢከሰት ህይወታችንን ይታደገናል ብለን ነው። ስታቲንም የሚረዳው እንዲሁ ነው፤ ወደፊት ድንገት ሳናስበው ሊከሰት የሚችል የልብ ድካም ወይም ስትሮክ እንዳይመታን ነው። ስታቲን የምንወስደው የአጭር ጊዜ ጤና መሻሻል ጠብቀን ሳይሆን ሳይጠበቅ ከሚመታ የማይታይ የደም ስር ችግር ለመከላከል ነው።
ማጠቃለያ
ስታቲኖች በዘመናችን የልብ ህክምና ሳይንስ ውስጥ በጥልቀት የተጠኑ፣ ፈውስነታቸውና ደህንነታቸው የተረጋገጠ መድሃኒቶች ናቸው። ስለሆነም ስታቲን ያስፈልገወታል ተብለው በሃኪም ከታዘዘለዎት በአግባቡ ይውሰዱ። ምንጩ በማይታወቅ የማህበራዊ ሚዲያ የወሬ ማእበል ተታላችሁ ልባችሁን አደጋ ላይ አንዳትጥሉ። የኮሌስትሮል መድሃኒትን ካለሃኪም ትእዛዝ ማቆም አደገኛ የጤና ቀውስ ሊያስከትል ይችላል። ስታቲን የልብዎት የደህንነት ቀበቶ ነው – ካልታሰበ የልብ አደጋ የሚከላልከል።
ዋቢ፡ International Atherosclerosis Society Bi-monthly Newsletter May-June 2025
ማስታወሻ፦ በዚህ መጣጥፍ ላይ የተካተቱት ሀሳቦች ለአጠቃላይ መረጃ ብቻ ናቸው። ለግል ምርመራ ወይም ህክምና ዶ/ር መላኩ ጋር በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስኳር ህክምና ክፍል መመካከር ይችላሉ።
በመረጃ የተደገፉና የተረጋገጡ ተግባራዊ የጤና ምክሮችን በዶ/ር መላኩ Blog, Telegram, YouTube & Tiktok ይከታተሉ።
ጥያቄ፣ እርምት ወይም ግብረ መልስ ካለዎት በዚህ አድራሻ ሊንክ ይጻፉልኝ።
ይህን መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ለሌሎች ያጋሩ።
‘ስታቲን መድሃኒት ስራዉን ሲሰራ እንደመኪና ላይ የደህንነት ቀበቶ ነው። ሁሌም መኪና ስንነዳ ወይም ስንሳፈር የደህንነት የመቀመጫ ቀበቶ ማሰር ይገባል አይደል? ይህን የምናደርገው መንገዱ ሳይመች ሲቀር፣ ስንደነቃቀፍ ወይም ገደል አፋፍ ስንደርስ ብቻ አይደለም፤ ሁሌም ቀበቶ ማሰር ግድ ነው። እጋጫለሁ በሚል ፍርሃት ሳይሆን ከስንት አንዴም ቢሆን ድንገት አደጋ ቢከሰት ህይወታችንን ይታደገናል ብለን ነው። ስታቲንም የሚረዳው እንዲሁ ነው፤ ወደፊት ድንገት ሳናስበው ሊከሰት የሚችል የልብ ድካም ወይም ስትሮክ እንዳይመታን ነው። ስታቲን የምንወስደው የአጭር ጊዜ ጤና መሻሻል ጠብቀን ሳይሆን ሳይጠበቅ ከሚመታ የማይታይ የደም ስር ችግር ለመከላከል ነው’ it is a good analogy and easy to undersatnd. thnk you dr
Hello, I am a 20yo female. I have had irregular periods since menarche at the age of 14. I went to many gynecologists starting from the age of 14 and they were prescribing OCPs and Progestins to regulate it without confirming the diagnosis with ultrasound. Later at the age of 19 I went to another gynecologist with an issue of irregular periods and he ordered an ultrasound imaging and used the ultrasound imaging and Rotterdam criteria and discovered that I have PCOS.
Then again he ordered to me Progestins, but still no change in period irregularity.
After knowing that I have PCOS I started reading articles and read that it causes or is caused by insulin resistance and LH/FSH levels disproportion. I read that ~50% of people with PCOS become diabetic by the age of 40. And went to another gynecologist to check for the presence of insulin resistance. He made fasting glucose lab test, and found to be in the normal range. And told me to leave it, because for an issue of fertility since there is medication to make it possible, since I am student now, he told me that I can go to gynecologists when I want to concieve in the future. He told me that the gynecologic aspect of PCOS is treatable. But I am worried about the metabolic/hormonal aspect of PCOS. I am not sure whether insulin resistance or other hormonal issues caused my PCOS. I feel like I have to consult an endocrinologist and I found your contact online.
I have all symptoms of pcos (acne, diffuse hairfall, mild hirsutism, irregular periods, mood disturbances) including multiple ovarian cysts on ultrasound, but no weight gain at all constant weight for years, healthy BMI and I am thin plus I am normoglycemic.
When I read, people who have insulin resistant PCOS are able to reverse not only their insulin sensitivity but also the entire hormonal and metabolic disturbances by taking the myo:dchiro 40:1 inositol supplement. This supplement is established in researches that is successful to reverse all PCOS symptoms and significantly decrease the incidence of insulin resistance and diabetes.
Should I take the 40:1 inositol supplement? Is there any lab test needed before taking this supplement?
Before using this supplement I knew that I have to consult an endocrinologist to help me assure my full metabolic and hormonal conditions so that my case is not a blind decision.
I went to 3 gynecologists but 3 of them ordered ultrasound, blood glucose & CBC. For the most part, they are diagnosing and treating the gnecological aspect i. e. Irregular periods because my blood glucose is normal, but from PMOS, while all other symptoms are present, as a student, what is affecting me the most in my daily life is the fatigue and sleepiness all the time, mood swingings and anxiety. Different from the doctors I mentioned above, what sorts of other lab diagnoses can you order to me if I come to your hospital to treat me?
Plus I heard reviews from myo:dchiro 40:1 inositol users that it reverses most of the symptoms of PMOS including fatigue, and is there any lab test ordered/needed before taking this supplement?
If you’re in a clinical setting where diagnosing and treating PMOS is possible, please let me know your hospital’s location and your availability.
Doctor please help me out.
Thanks🙏