የካልዲና ፔምበርተን ሕይወት፤ የመመራመር ጉጉት የወለደው ስኬት
ዘር፣ ቀለም፣ ባህል፣ ሃይማኖት ሳይገድበው በሁሉም የዓለም ጥግ ሁሉ የሚታወቅ መጠጥ በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። አንዱ ኮካ ኮላ እንደሆነ ጥርጥር የለኝም። ከውሃ፣ ሻይና ቡና ቀጥሎ በአያሌው የሚጠጣ አለማቀፋዊ መጠጥ ኮካ ነው። ኮካ ከመጠጥ በላይ ኢኮኖሚያዊ ፈጠራም ነው። በሁሉም አለማት ንፍቀ ክበብ ወደሁለት ቢሊዮን የሚጠጋ ኮካ መጠጥ በየቀኑ ይጨለጣል። የኮካን ቀይ እና ነጭ አርማ አይቶ የማይለይ…