ፕሮላክቲኖማ (Prolactinoma)
ፕሮላክቲን (Prolactin) ሆርሞን ምንድን ነው? ፒቱታሪ እጢ (pituitary gland) አንጎላችን ውስጥ የሚገኝ ትንሽ መጠን ያለው አተር የሚያክል ሆርሞን የሚያመነጭ የአካል ክፍላችን ነው። በርካታ ጠቃሚ ሆርሞኖችን ያመነጫል። የሚያመነጫቸው ሆርሞኖች የበርካታ ሌሎች የሆርሞን የሚያመነጩ እጢዎችን ተግባር ይቆጣጠራል። ፒቱታሪ እጢ ሆርሞኖችን አምርቶ በቀጥታ ወደ ደም ውስጥ ይለቃል። ከዚያም እንቅርትና ሌሎችም የምናውቃቸው የሆርሞን አመንጭ ክፍሎቻችን በርካታ አስፈላጊ ሆርሞኖችን…