A Tale of Kaldi’s Dancing Goats at Emory University
በሃገረ አሜሪካ የጆርጅያ ግዛት አትላንታ የሚገኘው ዝነኛው የኤሞሪ ዩኒቨርሲቲ ቅጽር ግቢ ዋነኛ ካፌዎች መካከል በሮሊንስ የማህበረሰብ ጤና ት/ቤት የሚገኘው ‘Dancing Goats’ እና በተማሪዎች መዝናኛ ማእከል ያለው ‘Kaldi’ ቡና ይጠቀሳሉ። የካፌዎችን ስም እንዳየሁ የኢትዮጵያ የቡና መፍለቂያ ምድርነት ታሪክ ልቤን አሞቀው። እረኛው ካልዲ (Kaldi) በከፋ አምባዎች ላይ ፍየሎቹን በለመለመ መስክ ሲያሰማራ ቡና ላይ የመጀመሪያዉን ጥናታዊ ምርመር ጀመረ።…