ለህመም ማስታገሻነት የስቴሮይድ መድሃኒቶችን በተደጋጋሚ ይወስዳሉ?

መልስዎ አዎ ከሆነ እነዚህ መድሃኒቶች ከተረጋገጠ የህክምና ተዛዝ ውጭ በሚወሰዱበት ጊዜ ለከፋ የጤና ችግር ያጋልጣሉ።
ጤና ይስጥልኝ፣ ዶ/ር መላኩ እባላለሁ። በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስኳርና ሆርሞን ህክምና እናንተን በማገልገል ላይ እገኛለሁ።
በዚህ ትምህርታዊ ጽሁፍ ካላአግባብ እና over-the-counter ስለሚወሰዱ የስቴሮይድ መድሃኒቶች የሚያስከትሉትን የጤና ጠንቅ እናወራለን።
Glucocorticoids የሚባሉት የመድሃኒት አይነቶች ለተለያዩ የኢንፍላሜሽን፣ አለርጂ፣ አርትራይትስና ሌሎች በርካታ ህመም አይነቶች ለማከም ጥቅም ላይ ይውላሉ።
የሚዋጥ ታብሌቶች፣ ቆዳ ላይ የሚቀቡ ቅባቶች፣ ጠብታ እና አንዲሁም በደም ስር የሚሰጡ መርፌዎችን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ሊታዘዙ ይገኛሉ።
ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀም አደጋዎች ያመጣል።
• ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀም ሲባል ያለ አሳማኝ የህክምና ተዛዝ ወይም ስፔሻሊስት ሃኪም ክትትል እነዚህን መድሃኒቶች መውሰድን ያመለክታል። እንዚህን መድሃኒቶች ለረዥም ጊዜ መውሰድ ከባድ የጤና እክል ያመጣል።
• አደገኛ የሆርሞን መዛባት የሚያስከትል cushing syndrome ያጋልጣል።
• ከመጠን ያልፈ ውፍረት ሊያመጣ ይችላል
• የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣
• የአጥንት መሳሳትና አደገኛ ስብራት ያስከትላል።
• የቆዳ መሳሳትና ለኢንፌክሽን መጋለጥ
ስለሆነም እንዚህን መድሃኒቶች ከተረጋገጠ የህክምና ትእዛዝ ዉጭ የሚወስዱ ከሆነ አሁኑኑ ተገቢውን ምክር ያግኙ ይመርመሩ።
በእነዚህና መሰል የሆርሞን ህክምና ለማግኘት፣ ለማማከርና ለመመርመር ወደ ዚህ ቻናል ይከታተሉ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top