የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት እርግዝና ላይ ያለው ተጽእኖ

የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት እርግዝና ላይ ያለው ተጽእኖ

የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት እርግዝና ላይ ያለው ተጽእኖ


ጤና ይስጥልኝ። ዶ/ር መላኩ ታዬ ነኝ። በዚህ ጽሁፍ የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት እርግዝና ላይ ስላለው ተጽእኖ እናነሳለን።


አንገት ፊት ለፊት ላይ የሚገኘው የታይሮይድ እጢ የሚያመነጫቸው ሆርሞኖች ለአጠቃላይ ጤንነት በተለይም ለጤናማ እርግዝና ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ (ሃይፖታይሮዲዝም)ም ሆነ የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት (ሃይፐርታይሮዲዝም) ለመሃንነት ሊዳርጉ ይችላሉ። በእርግዝና ጤና  ላይም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።


ሃይፖታይሮዲዝም መሃንነትን ሊያስከትል ይችላል።  ሆርሞኑ በትክክል ሳይታከም እርግዝና ከተከሰተም በርካታ የእርግዝና ችግሮችን የመጋለጥ እድልን ይጨምራል። ለአብነትም፤

•            ውርጃ፡ በተለይም በእርግዝና መጀመሪያዎች ሶስት ወራት ውስጥ ውርጃ ያመጣል። የጽንሱ የአካልና አእምሮ እድገት ይጎዳልል።

•            ያለቀኑ መወለድ፡- ሃይፖታይሮዲዝም ጽንሱ 9 ወር ሳይሞላው ካለጊዜው የመውለድ እድልን ይጨምራል።

•            ከፍተኛ የእርግዝና ጊዜ የደም ግፊት መጨመር (pre-eclampsia) እና ስኳር ህመም ያስከትላል።

•            በህፃኑ አእምሮ እድገት ላይ ተጽእኖ ያደርጋል። የሚወለደው ልጅ IQ ዝቅ እንዲል ሊያደርግ ይችላል።


የታይሮይድ ሆርሞን መብዛትም (ሃይፐርታይሮዲዝም) እንዲሁ የራሱ ችግሮች አሉት። የእርግዝና ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ልክ እንደ ሃይፖታይሮዲዝም ያልታከመ ሃይፐርታይሮዲዝም ከመሃንንነት እስከ ውርጃ ሊያመጣ ይችላል። በእናትዬዋ ላይ ከሚያስከትላቸው የጤና ችግሮች መካከል ከእርግዝና ጋር በተያያዙ የደም ግፊት፣ የልብ ምት ችግሮች እና ሌሎች ከባድ ችግሮች የመጋለጥ እድሏን ይጨምራል።


ያልታከመ የታይሮይድ ሆርሞን ማነስም ሆነ መብዛት እንዲህ ጣጣ ካለው እንዴት አስቀድመን እንከላከለው?


ለአብኛዎቹ ሴቶች ቅድመ እርግዝና የታይሮይድ ምርመራ ማድረግ ይመከራል። ይህም አስፈላጊ ህክምና ከእርግዝና ከመከሰቱ በፊት በትክክል እንዲታከም ያስችላል። ለእናትም ለህፃኑም ጤንነት አስተማማኝ የሆርሞን መጠን ከሆኑ በኋላ እርግዝና ቢመጣ ይሻላል።

ከእርግዝና በፊትም ሆነ በእርግዝና ጊዜ እንዲሁም ድህረ ወሊድ ስለታይሮይድ ጤንነትዎ የሚያሳስብዎት ነገር ካለ የሆርሞን ሃኪም ከሆኑት ዶ/ር መላኩ ታዬ ጋር በጥቁር አንበሳ ሆስፒታ ወይም በትርፍ ጊዜ በሚሰሩባቸው የግል ሆስፒታሎች ይመካከሩ።


የእርስዎን የታይሮይድ ጤንነት እንዴት መጠበቅ እንዳለብን በጥልቀት ስለምንማማር የሆርሞን ስፔሻሊስት ሃኪም መላኩን በwww.melakutaye.com, በቲክቶክና ቴሌግራም @hakimmelaku  ይከታተሉን።

ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት እባክዎን ላይክና ሼር ያድርጉ። በቀጣይ የጤና መረጃ እስክንገናኝ ጤና ይስጥልን።


Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top