ግለሰቡን ያማከለ የውፍረት ህክምና፡ ለሁሉም የሚስማማ አንድ ቀመር የለም!
ስለውፍረት ህክምና ያለን አረዳድ ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ ሲሆን ይታያል። ውፍረትን በጣም አቅሎ ማየትም አለ። አልፎ ተርፎም ወቃሽና አግላይ ሊሆን ይችላል። ለብዙዎች ውፍረት ሲባል በስንፍና ምክንያት የሚመጣ፣ ከግለሰቡ የግል ፍላጎት ማጣት ወይም ክብደትን ለማስተካከል አለመፈለግ ይመስላቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ ግለሰቦች ብዙ ወራት በራሳቸው ሞክረው የተለያዬ ምግብ አንስተው ጥለው፤ ጂም ደክሞው አልሳካ ሲላቸው ነው ለውፍረት ህክምና ወደባለሙያ የሚያቀኑት።…