የአርቲፊሻል ስኳር ጣፋጭነት እና መራራ የጤና ስጋቶች
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ‘ይሄን እንዳትበላ፣ ያንን እንዳትነካ’ የምግብ ክልከላዎች የምግብ አማራጮችን ወስነው የጣመ እንዳንመገብ እየገዘቱ ዉሃ ዉሃ የሚል ምግብ ብቸኛ ምርጫችን እንዲሆን እያስገደዱን ነው። ምላሳችን የሚቀምሰው ምግብ ሁሉ ጣእም አልባ እየሆነበት ነው። ይሄንን ጣእም የራቀው ማእድ ወደለመድነው ጣፋጭነት ለመመለስ እንዱ እማራጭ ካሎሪዎችን ሳይጨምሩ ጣፋጭነትን ማጣጣም የሚያስችሉ የስኳር ምትክ የሆኑ አርቲፊሻል ስኳር መዘውተር…