ጤናማ የተመጣጠነ ማእድ

ለስኳር፣ ውፍረት ወይም ኮሌስትሮል ህክምና የሚመጡ ታካሚዎች ስለአመጋገባቸው የሚያጋሩኝ ታሪኮች ከሞላ ጎደል ተመሳሳይነት አላቸው። ስለአመጋገብ ልማዳቸው ስጠይቃቸው ‘ኧረ እንዲያው ጥሎብኝ እንጅ ስኳር ከየት አግኝቼ አብዝቼ?’ በሚል ብስጭት የሚመልሱልኝም አሉ። እንደምንም ተረጋግተው ሲዘረዝሩት ግን ‘ለቁርስ ግማሽ ፍርፍር በግማሽ እንጀራና አንድ መለስተኛ የገብስ ዳቦ ብቻ ነው የምበላው‘  ይጀምሩና ‘ረፋድ ላይ ለቡና ቁርስ መዳፍ የምታክል ቂጣ ከቆሎ ጋር…