ኮሌስትሮል ለጤና ጎጂ ነውን?

በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ ጤና ነክ ‘አሉሽ አሉሽ ወሬዎች’ መካከል ‘ኮሌስትሮል የጤና ጉዳት አያመጣም እንዲያዉም ሊጠቅም ይችላል’ የሚል አሳች መረጃ ይገኝበታል። ‘ደግሞስ እንደኢትዮጵያ ያለ ገና በቀን ሶስቴ መብላት እውን ላልሆነበት ሃገር፣ ጮማ ሳንቆርጥ? ቅቤ ሳንጠጣ? የምን ኮሌስትሮል ነው?!’ የሚሉም አይጠፉም። ይህ አስተሳሰብ የኮሌስትሮል ችግርን ጮማ የሚያዘወትሩ፣ ውፍረት የሚያጠቃቸው የአደጉ ሃገሮች በሽታ ብቻ አድርጎ የመቁጠር የተሳሳተ ግንዛቤ…