አቮካዶ ለስኳር ህክምና ተስማሚ የሆነ ምግብ
ስለአቮካዶ የሚነሱ የተሳሳቱ ወሬዎች በየእለቱ የስኳር ታካሚዎችን አመጋገብ ስገመግም ከምሰማቸው ልማዶች ውስጥ አንዱ ‘አቮካዶ ለኮሌስትሮል ጎጂ እንደሆነ ስለሰማሁ አቮካዶ መብላት ካቆምኩ ዘመናት አልፈዋል‘ የሚል በሳይንስ ያልተደገፈ መረጃ ይጠቀሳል። አቮካዶ በያዘው የቅባት ይዘት ምክንያት ‘ለልብ ጤና ጎጂ ነው’ የሚል ከእውነት የራቀ መረጃ በስፋት ይሰማል። በአቮካዶ ውስጥ ያለው ቅባት ኮሌስትሮል ይጨምራል የሚባለው ወሬ ትክክለኛ አይደለም። ይህ የተሳሳተ…