የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ (Lifestyle) ለኮሌስትሮል ህክምና ያለው ሚና

ኮሌስትሮልን ለመቆጣጠር መድሃኒት መውሰድ ብቻ በቂ አይደለም። ይልቁንም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎችን ማዘውተር ኮሌስትሮልና ከኮሌስትሮል ጋር የተያያዙ የልብና የደም ስር ህመሞችን ለማከም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ጥሩነቱ አባዛኛዎቹ ለኮሌስትሮል ህክምና የሚመከሩ የአኗኗር ለውጥ መፍትሄዎች በቀላሉ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ ናቸው። ጤናማ የአኗኗር ዘዬ መከተል፣ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲሁም አልኮል መጠጥ መቀነስ ለኮሌስትሮል ህክምና መሰረታዊ ናቸው።  በዚህ…