ውፍረት እንደ አንድ ህመም ይታወቅ (diagnose obesity as a disease)
በአለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፉ የሚገኙትን የስኳር ህመምና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በፍጥነት መጨመር ዋነኛ ተቀዳሚ ምክንያት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ነው። እንደወረርሽኝ ስርጭታቸው እየጨመረ የመጡት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሁሉ ከጀርባ ያለው ግንባር ቀደም ድብቅ ምክንያት ውፍረት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ውፍረት የበሽታዎች ሁሉ እናት ነው ብለው የሚጠሩትም አሉ። ውፍረት ዓለም አቀፍ የጤና ቀውስ ነው። በአጠቃላይ ከአንድ…