ክብደት መቀነስ ለምን ቀላል አይሆንም – ከበስተጀርባ የሚታገሉን ድብቅ ሆርሞኖች!

በዶ/ር መላኩ ታዬ (በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስኳርና ውፍረት ህክምና ስፔሻሊስት)   እስቲ አስቡት አመጋገብ አስተካከለው፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወጥረው ሰርተው ከወራት እልህ አስጨራሽ ልፋት በኋላ ቦርጭን ልክ አስገባችሁት እንበል። በዚህ ስኬት ደስታና ፈንጠዝያ ይሆናል። በሰራችሁት አስደናቂ ተግባር ኩራት ይሰማችኋል። ግን ሰብሰብ ያለውን ወገብ ‘እኔ እኮ እችላለሁ፤ 8 ቁጥር ሽንቅጥ አልኩ እኮ!’ አድንቀው ሳይጨርሱ አንድ…