የእግር ጉዞ ማዘውተር ጤናን ያለመልማል
አዘውትሮ መራመድ ከተቻለ መሮጥ ለተሻለ ጤና ጉልህ ሚና ይጫወታል። እርምጃ ለአካላዊና አእምሯዊ ጤናን እንደሚፈውስ የተረጋገጠ ለሁላችን የተሰጠን ጸጋ ነው። በዚህ ጽሁፍ በእግር መጓዝ የሚሰጠንን የጤና በረከቶች እንዳስሳለን። እየተራመድን! አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልማድ እንዲሆንብን ማድረግ ይገባል። እኔ በበኩሌ ወክ ማድረግ አብሶ መሮጥ ሱስ ሆኖብኛል ብል ማጋነን አይሆንም። ሲደክመኝ መሮጥ ነው የማስበው፤ ስራ ጫና ሲበዛ ራመድ ራመድ…