ከወሊድ በኋላ የሚደረግ የስኳር ክትትል
የእርግዝና ወቅት ስኳር ህመም የተገኘባቸው ብዙ እናቶች ከወሊድ በኋላ እርግፍ አድረገው ይረሱታል። ‘ዶክተሬ ከወሊድ በኋላ ስኳር ይስተካከላል ስላለኝ ተውኩት’ የሚል ንግግር መስማት የተለመደ ነው። አራስ ልጅ መያዝና መንከባከብ በራሱ በጣም አድካሚ ስራ ስለሆነ ብዙ እናቶች ስለራሳቸው ጤና ለማሰብ ጊዜም አያገኙ። ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር የእርግዝና ጊዜ ስኳር ክትትል ከወሊድ በኋላ አያበቃም። የእርግዝና ጊዜ ስኳር የተገኘባት…