የኮሌስትሮል ምርመራ የሚሰራው በባዶ ሆድ ብቻ ወይስ በማንኛውም ጊዜ?
በዶ/ር መላኩ ታዬ በደም ውስጥ የሚገኙትን የኮሌስትሮል እና ትራይግሊሪይድ መጠን የሚለኩ ምርመራዎች የልብና የደም ስር ጤናን ለመለካት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ይህ ምርመራ በተለምዶ በባዶ ሆድ ብቻ ነው የሚሰራው የሚል ልማድ አለ። በተለይም አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች ረፋድ 3 ሰአት አካባቢ ካለፈ የኮሌስትሮል ምርመራ ‘አይሰራም፤ አልሰራም’ ብለው ተገልጋዩንም ምርመራውን ያዘዘውን ባለሙያም ሲያመናጭቁ አስተውያለሁ። ልክ ነው በቀደመው የህክምና…