የኮሌስትሮል ህመም የሀብታሞች ወይም የጮማ ሥጋ ለሚመገቡ ሰዎች ብቻ እንዳልሆነ ያውቃሉ?
የኮሌስትሮል ህመም የሁሉም ሰው ጉዳይ እንጂ ጮማ ለሚበሉ ሀብታሞች ወይም ቦርጭ ላላቸው ብቻ አይደለም! ማንኛውንም ሰው ሊያጠቃ ይችላል — አንተ/ችንም ጭምር! በየእለቱ የህክምና ስራዬን አዳጋች ከሚያደርጉብኝ ተግዳሮቶች መካከል አንደኛው በተለምዶ የኮሌስትሮል ህመም እና ተያያዥ የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች በሀብታሞች፣ ቦርጭ ባላቸው ግለሰቦች ወይም ጮማ ስጋ የሚያዘወትሩ ሰዎችን ብቻ የሚያጠቃ በሽታ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ነው።…