cholesterol

በህጻናት እና ልጆች ላይ የሚከሰት የኮሌስትሮል ህመም

ስለ ኮሌስትሮል ህመም ስናስብ ብዙውን ጊዜ ከአዋቂዎች ጋር ብቻ እናያይዘዋለን። ነገርግን ይህ የጤና ጉዳይ ህጻናትን እና ታዳጊዎችን ሊያጠቃ ይችላል። በዋናነት ልጆች ላይ የሚከሰት የኮሌስትሮል ህመም አይነቶች በዘር የሚተላለፉ ሲሆኑ በተጨማሪም ከአመጋገብ መዛባትና እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማነስ ጋር በተያያዘም የልጆች ኮሌስትሮል ሊዛባ ይችላል። በልጆችና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች የኮሌስትሮል ህመም በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ…

የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ (Lifestyle) ለኮሌስትሮል ህክምና ያለው ሚና

ኮሌስትሮልን ለመቆጣጠር መድሃኒት መውሰድ ብቻ በቂ አይደለም። ይልቁንም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎችን ማዘውተር ኮሌስትሮልና ከኮሌስትሮል ጋር የተያያዙ የልብና የደም ስር ህመሞችን ለማከም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ጥሩነቱ አባዛኛዎቹ ለኮሌስትሮል ህክምና የሚመከሩ የአኗኗር ለውጥ መፍትሄዎች በቀላሉ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ ናቸው። ጤናማ የአኗኗር ዘዬ መከተል፣ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲሁም አልኮል መጠጥ መቀነስ ለኮሌስትሮል ህክምና መሰረታዊ ናቸው።  በዚህ…

የኮሌስትሮል ህመም ምንነትና መንስኤዎች

የደም ቅባት መጠን መዛባት (Dyslipidemia) የሚባለው ህመም የደም ውስጥ የኮሌስትሮል ወይም ስብ መጠን ከተለመደው ውጭ ሲዛባ እና ይህም የልብና የደም ሥር በሽታዎች ታጋላጭነትን ሲጨምር የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ በሽታ ነው። በአኗኗር ዘይቤዎች መዛባት ወይም በዘር ተጋላጭነት የሚከሰት ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለልብ ሕመም ከሚዳርጉ ምክንያቶች አንዱ ነው። የደም ስር ቧንቧዎች ውስጥ በመከማቸት እንዲዝጉና እንዲደፈኑ በማድረግ  ወደልብ፣…

የደም ቅባት (Lipids)

ብዙዎቻችን የደም ቅባት (lipids)፣ ስብ (fat) ወይም ኮሌስትሮል (cholesterol) የሚል ነገር በተደጋጋሚ እንሰማለን። ለመሆኑ በትክክል ምንድን ናቸው? አንድነትና ልዩነታቸው ምንድን ነው? እነኚህ ቃላት ስንጠቀም አንዱ ሌላውን ሊተካ ይችላል ወይ? ከቃላት ትርጓሜ ባሻገር ስለደም ቅባት ማወቅ ለምን አስፈለገ? በዚህ መጣጥፍ ከደም ቅባት ጋር በተያያዘ ለጤናዎ እንክብካቤ የሚሆኑ ተግባራዊ ምክሮችን የመጀመርያ ክፍል እናቀርባለን። የደም ቅባቶች ስብነት ያላቸው…

የኮሌስትሮል ምርመራ የሚሰራው በባዶ ሆድ ብቻ ወይስ በማንኛውም ጊዜ?

በዶ/ር መላኩ ታዬ በደም ውስጥ የሚገኙትን የኮሌስትሮል እና ትራይግሊሪይድ መጠን የሚለኩ ምርመራዎች የልብና የደም ስር ጤናን ለመለካት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ይህ ምርመራ በተለምዶ በባዶ ሆድ ብቻ ነው የሚሰራው የሚል ልማድ አለ። በተለይም አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች ረፋድ 3 ሰአት አካባቢ ካለፈ የኮሌስትሮል ምርመራ  ‘አይሰራም፤ አልሰራም’ ብለው ተገልጋዩንም ምርመራውን ያዘዘውን ባለሙያም ሲያመናጭቁ አስተውያለሁ። ልክ ነው በቀደመው የህክምና…

የኮሌስትሮል ምርመራ፡ ለማን፣ መቼ እና ትክክለኛ መጠን?

ኮሌስትሮል ለልብና የደም ስር የጤና ችግሮች አንዱና ዋነኛው መንስኤ ነው። የኮሌስትሮል ምርመራ ከደም ናሙና የሚሰራ ሲሆን የኮሌስትሮል መጠን በትክክለኛው መጠን ውስጥ መሆኑን ለማወቅ አይነተኛ መንገድ ነው። በዚህ ጽሑፍ ስለ ኮሌስትሮል ምርመራ ማወቅ ያለብዎትን መሰረታዊ ጉዳዮች እናብራራለን – ምርመራው አስፈላጊነቱ ምንድን ነው? መቼ መመርመር አለብዎት? ምን ይታዘዛል? የምርመራ ውጤቱ ምን መምሰል አለበት?!   መቼ ነው የኮሌሌስትሮል…

Scroll to Top