diabetologist in ethiopia

የስኳር ታካሚዎችን ጤና ለማሻሻል አወንታዊ የጤና ልምዶችን መገንባት

የአሜሪካ የስኳር ማህበር (ADA) የስኳር ህመም ያለባቸው ግለሰቦች አወንታዊ የጤና ልምዶችን ማሳደግ ጤናን ለማሻሻል እንደ አንድ የህክምና ትኩረት አድርጎ አጽንዖት ይሰጣል። በየአመቱ የሚሻሻለው የስኳር ህክምና መመሪያ በምእራፍ አምስት የሚተነትነው ስለዚሁ ጉዳይ ነው። ይህም ግለሰቡን ያማከለ ሁለንተናዊ የባህሪ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ ያብራራል። ጤናማ ልማዶችን መገንባት እና የተሟላ ደህንነትን ያማከለ እንክብካቤ መስጠት የስኳር ህክምና ግቦችን ለማሳካት እንዲሁም…

ሙሉ ቀንዎትን በጥሩ ሁኔታ መምራት – እንቅስቃሴ፣ እረፍት፣ እንቅልፍ ማመጣጠን ለተሻለ ጤና

ብዙ ሰው የአንድ ሰአት ጂም ሰርቶ ቀሪውን  ሃያ ሶስት ሰአት ስለሚዘናጋ ጤናውን እንደሚፈለገው ማሻሻል አዳጋች ያደርገዋል። ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራት ከምናሳልፈው አጭር ጊዜ ባሻገር በሙሉ ቀን ውሎአችን የምናደርገው እንቅስቃሴ፣ እረፍትና እንቅልፍ ሁሉ ጤናን ይነካል። በታቀዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ወቅት ብቻ ሳይሆን በቀሪው ቀናችን የምንሰራው ስራ አጠቃላይ ጤና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር መገንዘብ ይገባል። የአሜሪካ የስኳር…

ለስኳር ታካሚዎች የፍራፍሬ አመጋገብ መመሪያ

የስኳር ታካሚዎች ከሚያነሷቸው መጠይቆች መካከል ‘ፍራፍሬ መመገብ እችላለሁ ወይ?’ የሚለው የተለመደ ጥያቄ ነው። የስኳር ታካሚዎች ፍራፍሬዎችን እንዴት መመገብ እንደሚችሉ በርካታ እርስ በእርስ የሚጣረሱ መረጃዎች ስለሚሰሙ ግራ መጋባት ይፈጥራሉ። ይህን ፍራፍሬ ብላ፣ ያንን ፍሬ እንዳትነካ፣ ይህ የተፈቀደ ነው፣ ያኛው ግዝት ነው ወዘተ የሚሉ ውዥንብር የሚፈጥሩ ያልተረጋገጡ የአመጋገብ ምክሮች አሉ። አንዱ ሃኪም አዎ ያለውን ሌላኛው አይ ብሎ…

ከአርቲፊሻል ስኳር ይልቅ በተፈጥሯዊ ማጣፈጫዎች ላይ እናተኩር

አርቲፊሻል ስኳር ማጣፈጫዎች ብዙውን ጊዜ እንደ ጤናማ አማራጭ ይቆጠራሉ። ሆኖም ግን  ስኳር ፍጆታን ለመቀነስ ቢረዱም ለተሻለ ጤና ዋስትና አይደሉም። የታሰበውን ጥቅም ላይሰጡ እንደሚችሉ አሊያም የጤና ጉዳት ሊያመጡ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ በርካታ የምርምር መረጃዎች እየወጡ ነው። አርቲፊሻል ስኳር ማጣፈጫዎች ምንም አይነት ምግብነት ወይም አልሚነት ጥቅም የላቸውም። አርቲፊሻል ስኳር ማጣፈጫዎችን እያስወገድን የበለጠ ጤናማ በሆኑ ተፈጥሯዊ ማጣፈጫዎች መቀየር በአጠቃላይ…

የስኳር ህመም፤ ችላ ልንለው የማንችለው ወረርሽኝ

የአለም የስኳር ህመም ሳምንትን እያከበርንበት ባለበት ሁኔታ ላይ በላንሴት የህክምና መጽሄት ላይ ዛሬ ታትሞ የወጣ አንድ ጥናት በስኳር ህመም ዙሪያ በቸልታ የማይታለፉ አሳሳቢ እውነታዎችን አስነብቧል። ይህ ሰፊ ጥናት ብዙ አስደንጋጭ መረጃዎችን ይዟል። በ200 አገሮች ውስጥ የሚገኙ ከ141 ሚሊዮን በላይ ወካይ ተሳታፊዎችን የሚያካትት ሆኖ ከ1,000 በላይ ጥናቶች የተውጣጡ መረጃዎችን የሚሸፍን ጥልቅ ትንታኔ ስለሆነ እስከዛሬ ከተሰሩ የዳሰሳ…

Scroll to Top