Diabetes

የስኳር ህመም ለሚታከሙ ሴቶች የቅድመ እርግዝና እንክብካቤ

ትክክለኛ ቅድመ እርግዝና የስኳር ህክምና እና ክትትል ማድረግ እርግዝና ጤናማ እንዲሆን ያስችላል፤ ልጅም ደህና እንዲወለድ ይረዳል። ጤናማ እርግዝና የሚጀምረው ከመፀነስሽ በፊት ነው። የቅድመ እርግዝና እንክብካቤ በጣም አስፈላጊ ነው። የስኳር ህመም ያለባቸው ሴቶች አስቀድመው ማቀድና ማስተካከያ ማድረግ ለተሻለ ውጤት ወሳኝ ነው። የጽንስ ጤና ችግሮች እንዳይከሰቱ ይረዳል። ስለሆነም የእርግዝና ጊዜን በደንብ ማሰብ ያስፈልጋል። የስኳር መጠኑ አሪፍ ቁጥጥር…

በእርግዝና ወቅት የሚደረግ የስኳር ቅድመ-ምርመራ ለሁሉም እናት (universal screening for Gestational diabetes)

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም (Gestational diabetes, GDM) ሲባል በእርግዝና ጊዜ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ ብሎ ሲገኝ የሚከሰት የጤና ችግር ሲሆን ነፍሰ ጡር እናቶችን ከሚያጠቁ የጤና ችግሮች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። በአብዛኛው  በ24 እና 28 ሳምንታት መካከል ባለው የእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኳር ህመም አይነት ነው። ይህ የስኳር አይነት ብዙውን ጊዜ ከወሊድ በኋላ…

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም የህክምና ግቦች (Treatment Targets for gestational diabetes: What Should You Aim For?)

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ ብሎ ሲገኝ የሚከሰት የጤና ችግር ሲሆን ነፍሰ ጡር እናቶችን ከሚያጠቁ የጤና ችግሮች በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በአብዛኛው ከ5-7 ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ የሚከሰትና ከወሊድ በኋላ የሚጠፋ የስኳር ህመም አይነት ነው። የእናት ጤንነት እና የጽንሱን ደህንነት ለማረጋገጥ ጥንቃቄ የተሞላበት የስኳር ህክምና…

የስኳር ታካሚዎችን ጤና ለማሻሻል አወንታዊ የጤና ልምዶችን መገንባት

የአሜሪካ የስኳር ማህበር (ADA) የስኳር ህመም ያለባቸው ግለሰቦች አወንታዊ የጤና ልምዶችን ማሳደግ ጤናን ለማሻሻል እንደ አንድ የህክምና ትኩረት አድርጎ አጽንዖት ይሰጣል። በየአመቱ የሚሻሻለው የስኳር ህክምና መመሪያ በምእራፍ አምስት የሚተነትነው ስለዚሁ ጉዳይ ነው። ይህም ግለሰቡን ያማከለ ሁለንተናዊ የባህሪ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ ያብራራል። ጤናማ ልማዶችን መገንባት እና የተሟላ ደህንነትን ያማከለ እንክብካቤ መስጠት የስኳር ህክምና ግቦችን ለማሳካት እንዲሁም…

ለስኳር ታካሚዎች የፍራፍሬ አመጋገብ መመሪያ

የስኳር ታካሚዎች ከሚያነሷቸው መጠይቆች መካከል ‘ፍራፍሬ መመገብ እችላለሁ ወይ?’ የሚለው የተለመደ ጥያቄ ነው። የስኳር ታካሚዎች ፍራፍሬዎችን እንዴት መመገብ እንደሚችሉ በርካታ እርስ በእርስ የሚጣረሱ መረጃዎች ስለሚሰሙ ግራ መጋባት ይፈጥራሉ። ይህን ፍራፍሬ ብላ፣ ያንን ፍሬ እንዳትነካ፣ ይህ የተፈቀደ ነው፣ ያኛው ግዝት ነው ወዘተ የሚሉ ውዥንብር የሚፈጥሩ ያልተረጋገጡ የአመጋገብ ምክሮች አሉ። አንዱ ሃኪም አዎ ያለውን ሌላኛው አይ ብሎ…

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም (Gestational diabetes)

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ ብሎ ሲገኝ የሚከሰት የጤና ችግር ነው። በአብዛኛው ከ5-7 ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ የሚከሰትና ከወሊድ በኋላ የሚጠፋ ነው። የስኳር ህመም በእርግዝና ወቅት ሲመጣ በነፍሰ ጡር እናቶች እና በጽንስ ጤና ላይ ተጽዕኖ ያስከትላል። ነገር ግን የስኳር ህመም በተገቢው መንገድ ከታከመ…

የስኳር ህመም፤ ችላ ልንለው የማንችለው ወረርሽኝ

የአለም የስኳር ህመም ሳምንትን እያከበርንበት ባለበት ሁኔታ ላይ በላንሴት የህክምና መጽሄት ላይ ዛሬ ታትሞ የወጣ አንድ ጥናት በስኳር ህመም ዙሪያ በቸልታ የማይታለፉ አሳሳቢ እውነታዎችን አስነብቧል። ይህ ሰፊ ጥናት ብዙ አስደንጋጭ መረጃዎችን ይዟል። በ200 አገሮች ውስጥ የሚገኙ ከ141 ሚሊዮን በላይ ወካይ ተሳታፊዎችን የሚያካትት ሆኖ ከ1,000 በላይ ጥናቶች የተውጣጡ መረጃዎችን የሚሸፍን ጥልቅ ትንታኔ ስለሆነ እስከዛሬ ከተሰሩ የዳሰሳ…

ህዳር 5 የአለም የስኳር ህመም ቀን፡ ምሉእ ደህንነትን ያስቀደመ የስኳር ህክምና እንክብካቤ

በዶ/ር መላኩ ታዬ (በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስኳርና ሆርሞን ህክምና ስፔሻሊስት) ‘የስኳር ህመም አለብህ/ሽ’ መባል በብዙዎች ልብ ውስጥ አስፈሪ ስሜት የሚፈጥር ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ያለ ተላላፊ ያልሆነ በሽታ ነው። በተለይም የዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች የስኳር ህመም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። በሃገራችን ኢትዮጵያ የተሰሩ ጥናቶች የሚያረጋግጡት ቁጥራቸው ላቅ…

የአይነት አንድ ስኳር ህክምና አሁናዊ መመሪያዎችና ተስፋ ሰጪ ምርምር ዉጤቶች

የአይነት 1 ስኳር ህመም (type 1 diabetes) ያለበት ልጅ ያላቸው ወላጆች ለልጃቸው ህክምና ተስፋ የሚሰጥ ዜና መፈለግ ያለ ነው። ወላጆች የልጃቸው ህይወት ከኢንሱሊን መርፌ ነፃ እንዲሆን መመኘታቸው ተፈጥሯዊ ነው። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ እነዚህ መሬት ያልያዙ ተስፋዎች አሳሳች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዴም አደገኛ የሆኑ አሳች ዜናዎች የልጅን ህይወት ሊቀጥፉ ይችላሉ። በዚህ ሳምንት በቲክቶክና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በጣም…

የአሳች ፈዋሾች ውሸት እንዴት መለየት ይቻላል?

በአለም አቀፍ እንዲሁም በኢትዮጵያ ደረጃ የስኳር ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል። በስኳር ህመም ዙርያ የሚነገሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችና አሳች ፈዋሾችም እንዲሁ እንደወረርሽኝ በስፋት ይታዩ ጀምረዋል። የስኳር በሽታን ለማዳን የሚሰጡ የባህል ህክምና ምርቶች እዚህም እዚያም ይሰማሉ። ይባስ ብሎም ብዙ ታዳሚ ያላቸው ጋዜጦችና ቴሌቪዥን ሚዲያ ተቋማት ሳይንሳዊ ማስረጃ የሌላቸው ጎጂ አፈ ታሪኮች እና የተሳሳቱ አመለካከቶች ማሰራጫና ነጻ…

Scroll to Top