Dr. Melaku Taye

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም (Gestational diabetes)

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ ብሎ ሲገኝ የሚከሰት የጤና ችግር ነው። በአብዛኛው ከ5-7 ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ የሚከሰትና ከወሊድ በኋላ የሚጠፋ ነው። የስኳር ህመም በእርግዝና ወቅት ሲመጣ በነፍሰ ጡር እናቶች እና በጽንስ ጤና ላይ ተጽዕኖ ያስከትላል። ነገር ግን የስኳር ህመም በተገቢው መንገድ ከታከመ…

ግለሰቡን ያማከለ የውፍረት ህክምና፡ ለሁሉም የሚስማማ አንድ ቀመር የለም!

ስለውፍረት ህክምና ያለን አረዳድ ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ ሲሆን ይታያል። ውፍረትን በጣም አቅሎ ማየትም አለ። አልፎ ተርፎም ወቃሽና አግላይ ሊሆን ይችላል። ለብዙዎች ውፍረት ሲባል በስንፍና ምክንያት የሚመጣ፣ ከግለሰቡ የግል ፍላጎት ማጣት ወይም ክብደትን ለማስተካከል አለመፈለግ ይመስላቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ ግለሰቦች ብዙ ወራት በራሳቸው ሞክረው የተለያዬ ምግብ አንስተው ጥለው፤ ጂም ደክሞው አልሳካ ሲላቸው ነው ለውፍረት ህክምና ወደባለሙያ የሚያቀኑት።…

ከአርቲፊሻል ስኳር ይልቅ በተፈጥሯዊ ማጣፈጫዎች ላይ እናተኩር

አርቲፊሻል ስኳር ማጣፈጫዎች ብዙውን ጊዜ እንደ ጤናማ አማራጭ ይቆጠራሉ። ሆኖም ግን  ስኳር ፍጆታን ለመቀነስ ቢረዱም ለተሻለ ጤና ዋስትና አይደሉም። የታሰበውን ጥቅም ላይሰጡ እንደሚችሉ አሊያም የጤና ጉዳት ሊያመጡ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ በርካታ የምርምር መረጃዎች እየወጡ ነው። አርቲፊሻል ስኳር ማጣፈጫዎች ምንም አይነት ምግብነት ወይም አልሚነት ጥቅም የላቸውም። አርቲፊሻል ስኳር ማጣፈጫዎችን እያስወገድን የበለጠ ጤናማ በሆኑ ተፈጥሯዊ ማጣፈጫዎች መቀየር በአጠቃላይ…

ከመጠን ያለፈ ውፍረት (obesity)

ውፍረት ማለት የሰውነት ስብ ከመጠን በላይ መብዛት ጋር የተያያዘ ስር የሰደደና የሚያገረሽ ውስብስብ በሽታ (Adiposity Based Chronic Disease) ነው። በተለምዶ የመጠነ ክብደት (body mass index) ከ30 በላይ ሲሆን ከመጠን በላይ ውፍረት ይባላል። ለከባድ የጤና ችግሮች የሚያጋልጥ ሲሆን ህክናምናዎቹ አመጋገብ ማስተካከል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን መጨመር፣ በመድሃኒትና የውፍረት ኦፕሬሽን የመሳሰሉ የህክምና አማራጮችን ያካትታሉ። የውፍረት አሳሳቢነት በአለም አቀፍና…

የአርቲፊሻል ስኳር ጣፋጭነት እና መራራ የጤና ስጋቶች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ‘ይሄን እንዳትበላ፣ ያንን እንዳትነካ’ የምግብ ክልከላዎች የምግብ አማራጮችን ወስነው የጣመ እንዳንመገብ እየገዘቱ ዉሃ ዉሃ የሚል ምግብ ብቸኛ ምርጫችን እንዲሆን እያስገደዱን ነው። ምላሳችን የሚቀምሰው ምግብ ሁሉ ጣእም አልባ እየሆነበት ነው።  ይሄንን ጣእም የራቀው ማእድ ወደለመድነው ጣፋጭነት ለመመለስ እንዱ እማራጭ ካሎሪዎችን ሳይጨምሩ ጣፋጭነትን ማጣጣም የሚያስችሉ የስኳር ምትክ የሆኑ አርቲፊሻል ስኳር መዘውተር…

የስኳር ህመም፤ ችላ ልንለው የማንችለው ወረርሽኝ

የአለም የስኳር ህመም ሳምንትን እያከበርንበት ባለበት ሁኔታ ላይ በላንሴት የህክምና መጽሄት ላይ ዛሬ ታትሞ የወጣ አንድ ጥናት በስኳር ህመም ዙሪያ በቸልታ የማይታለፉ አሳሳቢ እውነታዎችን አስነብቧል። ይህ ሰፊ ጥናት ብዙ አስደንጋጭ መረጃዎችን ይዟል። በ200 አገሮች ውስጥ የሚገኙ ከ141 ሚሊዮን በላይ ወካይ ተሳታፊዎችን የሚያካትት ሆኖ ከ1,000 በላይ ጥናቶች የተውጣጡ መረጃዎችን የሚሸፍን ጥልቅ ትንታኔ ስለሆነ እስከዛሬ ከተሰሩ የዳሰሳ…

ህዳር 5 የአለም የስኳር ህመም ቀን፡ ምሉእ ደህንነትን ያስቀደመ የስኳር ህክምና እንክብካቤ

በዶ/ር መላኩ ታዬ (በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስኳርና ሆርሞን ህክምና ስፔሻሊስት) ‘የስኳር ህመም አለብህ/ሽ’ መባል በብዙዎች ልብ ውስጥ አስፈሪ ስሜት የሚፈጥር ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ያለ ተላላፊ ያልሆነ በሽታ ነው። በተለይም የዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች የስኳር ህመም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። በሃገራችን ኢትዮጵያ የተሰሩ ጥናቶች የሚያረጋግጡት ቁጥራቸው ላቅ…

የአይነት አንድ ስኳር ህክምና አሁናዊ መመሪያዎችና ተስፋ ሰጪ ምርምር ዉጤቶች

የአይነት 1 ስኳር ህመም (type 1 diabetes) ያለበት ልጅ ያላቸው ወላጆች ለልጃቸው ህክምና ተስፋ የሚሰጥ ዜና መፈለግ ያለ ነው። ወላጆች የልጃቸው ህይወት ከኢንሱሊን መርፌ ነፃ እንዲሆን መመኘታቸው ተፈጥሯዊ ነው። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ እነዚህ መሬት ያልያዙ ተስፋዎች አሳሳች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዴም አደገኛ የሆኑ አሳች ዜናዎች የልጅን ህይወት ሊቀጥፉ ይችላሉ። በዚህ ሳምንት በቲክቶክና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በጣም…

Ulfaatina qaamaa hir’isuun maaliif salphaa miti – hormoonota dhokataa duubaan nu lolan!

Dr. Melaku Tayetiin (Hospitaala Ispeeshaalaayizd Tikur Anbessa keessatti ispeeshaalistii yaala dhukkuba Sukkaaraa fi Furdinna) Mee yaadadhaa, nyaata keessan erga sirreessitanii, sochii qaamaa erga gootanii, fi ji’ootaaf carraaqqii gootanii booda, cooma garaa(boorcii) gubdaniittu. Milkaa’ina kana keessatti gammachuu guddaatu jira. Hojii ajaa’ibaa hojjechaa jirtaniin ni boontu. Garuu mudhiin qalla’e tokko “An nan danda’a;  Mudhii lakkoofsa 8 argadheera!” jettanii…

ፕሮላክቲኖማ (Prolactinoma)

ፕሮላክቲን (Prolactin) ሆርሞን ምንድን ነው?   ፒቱታሪ እጢ (pituitary gland) አንጎላችን ውስጥ የሚገኝ ትንሽ መጠን ያለው አተር የሚያክል ሆርሞን የሚያመነጭ የአካል ክፍላችን ነው። በርካታ ጠቃሚ ሆርሞኖችን ያመነጫል። የሚያመነጫቸው ሆርሞኖች የበርካታ ሌሎች የሆርሞን የሚያመነጩ እጢዎችን ተግባር ይቆጣጠራል። ፒቱታሪ እጢ ሆርሞኖችን አምርቶ በቀጥታ ወደ ደም ውስጥ ይለቃል። ከዚያም እንቅርትና ሌሎችም የምናውቃቸው የሆርሞን አመንጭ ክፍሎቻችን በርካታ አስፈላጊ ሆርሞኖችን…

Scroll to Top