endocrinologist in ethiopia

ውፍረት እንደ አንድ ህመም ይታወቅ (diagnose obesity as a disease)

በአለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፉ የሚገኙትን የስኳር ህመምና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በፍጥነት መጨመር ዋነኛ ተቀዳሚ ምክንያት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ነው። እንደወረርሽኝ ስርጭታቸው እየጨመረ የመጡት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሁሉ ከጀርባ ያለው ግንባር ቀደም ድብቅ ምክንያት ውፍረት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ውፍረት የበሽታዎች ሁሉ እናት ነው ብለው የሚጠሩትም አሉ። ውፍረት ዓለም አቀፍ የጤና ቀውስ ነው። በአጠቃላይ ከአንድ…

ለስኳር ታካሚዎች የፍራፍሬ አመጋገብ መመሪያ

የስኳር ታካሚዎች ከሚያነሷቸው መጠይቆች መካከል ‘ፍራፍሬ መመገብ እችላለሁ ወይ?’ የሚለው የተለመደ ጥያቄ ነው። የስኳር ታካሚዎች ፍራፍሬዎችን እንዴት መመገብ እንደሚችሉ በርካታ እርስ በእርስ የሚጣረሱ መረጃዎች ስለሚሰሙ ግራ መጋባት ይፈጥራሉ። ይህን ፍራፍሬ ብላ፣ ያንን ፍሬ እንዳትነካ፣ ይህ የተፈቀደ ነው፣ ያኛው ግዝት ነው ወዘተ የሚሉ ውዥንብር የሚፈጥሩ ያልተረጋገጡ የአመጋገብ ምክሮች አሉ። አንዱ ሃኪም አዎ ያለውን ሌላኛው አይ ብሎ…

ከአርቲፊሻል ስኳር ይልቅ በተፈጥሯዊ ማጣፈጫዎች ላይ እናተኩር

አርቲፊሻል ስኳር ማጣፈጫዎች ብዙውን ጊዜ እንደ ጤናማ አማራጭ ይቆጠራሉ። ሆኖም ግን  ስኳር ፍጆታን ለመቀነስ ቢረዱም ለተሻለ ጤና ዋስትና አይደሉም። የታሰበውን ጥቅም ላይሰጡ እንደሚችሉ አሊያም የጤና ጉዳት ሊያመጡ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ በርካታ የምርምር መረጃዎች እየወጡ ነው። አርቲፊሻል ስኳር ማጣፈጫዎች ምንም አይነት ምግብነት ወይም አልሚነት ጥቅም የላቸውም። አርቲፊሻል ስኳር ማጣፈጫዎችን እያስወገድን የበለጠ ጤናማ በሆኑ ተፈጥሯዊ ማጣፈጫዎች መቀየር በአጠቃላይ…

የአይነት አንድ ስኳር ህክምና አሁናዊ መመሪያዎችና ተስፋ ሰጪ ምርምር ዉጤቶች

የአይነት 1 ስኳር ህመም (type 1 diabetes) ያለበት ልጅ ያላቸው ወላጆች ለልጃቸው ህክምና ተስፋ የሚሰጥ ዜና መፈለግ ያለ ነው። ወላጆች የልጃቸው ህይወት ከኢንሱሊን መርፌ ነፃ እንዲሆን መመኘታቸው ተፈጥሯዊ ነው። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ እነዚህ መሬት ያልያዙ ተስፋዎች አሳሳች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዴም አደገኛ የሆኑ አሳች ዜናዎች የልጅን ህይወት ሊቀጥፉ ይችላሉ። በዚህ ሳምንት በቲክቶክና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በጣም…

ፕሮላክቲኖማ (Prolactinoma)

ፕሮላክቲን (Prolactin) ሆርሞን ምንድን ነው?   ፒቱታሪ እጢ (pituitary gland) አንጎላችን ውስጥ የሚገኝ ትንሽ መጠን ያለው አተር የሚያክል ሆርሞን የሚያመነጭ የአካል ክፍላችን ነው። በርካታ ጠቃሚ ሆርሞኖችን ያመነጫል። የሚያመነጫቸው ሆርሞኖች የበርካታ ሌሎች የሆርሞን የሚያመነጩ እጢዎችን ተግባር ይቆጣጠራል። ፒቱታሪ እጢ ሆርሞኖችን አምርቶ በቀጥታ ወደ ደም ውስጥ ይለቃል። ከዚያም እንቅርትና ሌሎችም የምናውቃቸው የሆርሞን አመንጭ ክፍሎቻችን በርካታ አስፈላጊ ሆርሞኖችን…

የበለጸጉ ምግቦች (fortified foods) በኢትዮጵያ የምግብ ህግ

የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠቃል።  á‰ á‰°áˆˆá‹­áˆ የእናቶችና ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው። እንደ ብረት፣ ዚንክ እና ቫይታሚን ያሉ ለጤና አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እጥረት ከሲሶ እስከ ግማሽ ያክሉን የማህበረሰብ ክፍል የሚያጠቃ ሼር የሰደደ ድብቅ ረሃብ ነው። የእነዚህ የቪታሚኖች እና ማዕድናት እጥረት የአካል እና የአእምሮ እድገት…

የኮሌስትሮል ህመም የሀብታሞች ወይም የጮማ ሥጋ ለሚመገቡ ሰዎች ብቻ እንዳልሆነ ያውቃሉ?

የኮሌስትሮል ህመም የሁሉም ሰው ጉዳይ እንጂ ጮማ ለሚበሉ ሀብታሞች ወይም ቦርጭ ላላቸው ብቻ አይደለም! ማንኛውንም ሰው ሊያጠቃ ይችላል — አንተ/ችንም ጭምር! በየእለቱ የህክምና ስራዬን አዳጋች ከሚያደርጉብኝ ተግዳሮቶች መካከል አንደኛው በተለምዶ የኮሌስትሮል ህመም እና ተያያዥ የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች በሀብታሞች፣ ቦርጭ ባላቸው ግለሰቦች ወይም ጮማ ስጋ የሚያዘወትሩ ሰዎችን ብቻ የሚያጠቃ በሽታ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ነው።…

የኮሌስትሮል ህክምና ግብ (therapeutic targets of cholesterol treatment)

ለመሆኑ የልብና ተያያዥ የደም ሾር ህመም ስጋትን በአስተማማኝነት ለመቀነስ የሚረዳው የኮሌስትሮል ህክምና ግብ ምን መሆን አለበት? ኮሌስትሮልን በተገቢው ሁኔታ ማከም የልብን እና ተያያዥ የደም ሾር ህመሞችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ይረዳል። ከፍ ያለ የኮሌስትሮል መጠን በተለይም የጎጂ ኮሌስትሮል የሚፈለገውን ያክል ቁጥጥር ውስጥ አለመሆን ለልብ ድካም፣ ለስትሮክ እና ሌሎችም የደም ሾር ህመሞች ተጋላጭነት በእጅጉ እንደሚጨምር ያለጥርጥር የተረጋገጠ ሳይንስ…

በህጻናት እና ልጆች ላይ የሚከሰት የኮሌስትሮል ህመም

ሾለ ኮሌስትሮል ህመም ስናስብ ብዙውን ጊዜ ከአዋቂዎች ጋር ብቻ እናያይዘዋለን። ነገርግን ይህ የጤና ጉዳይ ህጻናትን እና ታዳጊዎችን ሊያጠቃ ይችላል። በዋናነት ልጆች ላይ የሚከሰት የኮሌስትሮል ህመም አይነቶች በዘር የሚተላለፉ ሲሆኑ በተጨማሪም ከአመጋገብ መዛባትና እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማነስ ጋር በተያያዘም የልጆች ኮሌስትሮል ሊዛባ ይችላል። በልጆችና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች የኮሌስትሮል ህመም በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ…

Scroll to Top