HEALTH

እርጣት (menopause)

ማረጥ የሴቶች ሆርሞን ኡደት አንዱ ምዕራፍ ነው። እርጣት የሚባለው የሴት የወር አበባ በቋሚነት የሚቆምበት ጊዜ ነው። ይህ የሚሆነው ኦቫሪ እንቁላልን ማምረት ማቆም ተከትሎ የሴት ሆርሞኖች (ኢስትሮጅን፣ ፕሮጀስትሮን) ስለሚቀንሱ ነው። የወር አበባ ሙሉ በሙሉ ከመቆሙ በፊት የሚቆራረጥበት የሽግግር ወራት/አመታት ሊኖሩት ይችላሉ። በአብዛኛው ከ45 እስከ 55 አመት እድሜ ላይ ይመጣል። የወር አበባ በእርግዝና፣ በህመም፣ በእርግዝና መከላከያ መድሃኒት…

የበለጸጉ ምግቦች (fortified foods) በኢትዮጵያ የምግብ ህግ

የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠቃል።  በተለይም የእናቶችና ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው። እንደ ብረት፣ ዚንክ እና ቫይታሚን ያሉ ለጤና አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እጥረት ከሲሶ እስከ ግማሽ ያክሉን የማህበረሰብ ክፍል የሚያጠቃ ሥር የሰደደ ድብቅ ረሃብ ነው። የእነዚህ የቪታሚኖች እና ማዕድናት እጥረት የአካል እና የአእምሮ እድገት…

የአሳች ፈዋሾች ውሸት እንዴት መለየት ይቻላል?

በአለም አቀፍ እንዲሁም በኢትዮጵያ ደረጃ የስኳር ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል። በስኳር ህመም ዙርያ የሚነገሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችና አሳች ፈዋሾችም እንዲሁ እንደወረርሽኝ በስፋት ይታዩ ጀምረዋል። የስኳር በሽታን ለማዳን የሚሰጡ የባህል ህክምና ምርቶች እዚህም እዚያም ይሰማሉ። ይባስ ብሎም ብዙ ታዳሚ ያላቸው ጋዜጦችና ቴሌቪዥን ሚዲያ ተቋማት ሳይንሳዊ ማስረጃ የሌላቸው ጎጂ አፈ ታሪኮች እና የተሳሳቱ አመለካከቶች ማሰራጫና ነጻ…

ክብደት መቀነስ ለምን ቀላል አይሆንም – ከበስተጀርባ የሚታገሉን ድብቅ ሆርሞኖች!

በዶ/ር መላኩ ታዬ (በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስኳርና ውፍረት ህክምና ስፔሻሊስት)   እስቲ አስቡት አመጋገብ አስተካከለው፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወጥረው ሰርተው ከወራት እልህ አስጨራሽ ልፋት በኋላ ቦርጭን ልክ አስገባችሁት እንበል። በዚህ ስኬት ደስታና ፈንጠዝያ ይሆናል። በሰራችሁት አስደናቂ ተግባር ኩራት ይሰማችኋል። ግን ሰብሰብ ያለውን ወገብ ‘እኔ እኮ እችላለሁ፤ 8 ቁጥር ሽንቅጥ አልኩ እኮ!’ አድንቀው ሳይጨርሱ አንድ…

የኮሌስትሮል ህመም የሀብታሞች ወይም የጮማ ሥጋ ለሚመገቡ ሰዎች ብቻ እንዳልሆነ ያውቃሉ?

የኮሌስትሮል ህመም የሁሉም ሰው ጉዳይ እንጂ ጮማ ለሚበሉ ሀብታሞች ወይም ቦርጭ ላላቸው ብቻ አይደለም! ማንኛውንም ሰው ሊያጠቃ ይችላል — አንተ/ችንም ጭምር! በየእለቱ የህክምና ስራዬን አዳጋች ከሚያደርጉብኝ ተግዳሮቶች መካከል አንደኛው በተለምዶ የኮሌስትሮል ህመም እና ተያያዥ የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች በሀብታሞች፣ ቦርጭ ባላቸው ግለሰቦች ወይም ጮማ ስጋ የሚያዘወትሩ ሰዎችን ብቻ የሚያጠቃ በሽታ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ነው።…

የኮሌስትሮል ህክምና ግብ (therapeutic targets of cholesterol treatment)

ለመሆኑ የልብና ተያያዥ የደም ስር ህመም ስጋትን በአስተማማኝነት ለመቀነስ የሚረዳው የኮሌስትሮል ህክምና ግብ ምን መሆን አለበት? ኮሌስትሮልን በተገቢው ሁኔታ ማከም የልብን እና ተያያዥ የደም ስር ህመሞችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ይረዳል። ከፍ ያለ የኮሌስትሮል መጠን በተለይም የጎጂ ኮሌስትሮል የሚፈለገውን ያክል ቁጥጥር ውስጥ አለመሆን ለልብ ድካም፣ ለስትሮክ እና ሌሎችም የደም ስር ህመሞች ተጋላጭነት በእጅጉ እንደሚጨምር ያለጥርጥር የተረጋገጠ ሳይንስ…

የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ (Lifestyle) ለኮሌስትሮል ህክምና ያለው ሚና

ኮሌስትሮልን ለመቆጣጠር መድሃኒት መውሰድ ብቻ በቂ አይደለም። ይልቁንም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎችን ማዘውተር ኮሌስትሮልና ከኮሌስትሮል ጋር የተያያዙ የልብና የደም ስር ህመሞችን ለማከም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ጥሩነቱ አባዛኛዎቹ ለኮሌስትሮል ህክምና የሚመከሩ የአኗኗር ለውጥ መፍትሄዎች በቀላሉ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ ናቸው። ጤናማ የአኗኗር ዘዬ መከተል፣ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲሁም አልኮል መጠጥ መቀነስ ለኮሌስትሮል ህክምና መሰረታዊ ናቸው።  በዚህ…

የደም ቅባት (Lipids)

ብዙዎቻችን የደም ቅባት (lipids)፣ ስብ (fat) ወይም ኮሌስትሮል (cholesterol) የሚል ነገር በተደጋጋሚ እንሰማለን። ለመሆኑ በትክክል ምንድን ናቸው? አንድነትና ልዩነታቸው ምንድን ነው? እነኚህ ቃላት ስንጠቀም አንዱ ሌላውን ሊተካ ይችላል ወይ? ከቃላት ትርጓሜ ባሻገር ስለደም ቅባት ማወቅ ለምን አስፈለገ? በዚህ መጣጥፍ ከደም ቅባት ጋር በተያያዘ ለጤናዎ እንክብካቤ የሚሆኑ ተግባራዊ ምክሮችን የመጀመርያ ክፍል እናቀርባለን። የደም ቅባቶች ስብነት ያላቸው…

Mee har’a furmaata qabatamaa bara haaraa fayya qabeessa ta’eef haa jalqabnu

Dr. Melaku Taye (Ogeessa Dhukkuba Sukkaaraa Hospitaala Ispeeshaalistii Tikur Anbessaa) tiin Fulbaanaan yommuu seenu baay’een keenya bara darbe caalaa jijjiirama gaarii jireenya keenya keessatti hojiirra oolchuuf kaka’umsa qabna;  Fayyaa ta’uu barbaanna. Fayyaan murtoo jalqabaa bara kana murteessuu qabnu (new year resolution)  keessaa isa tokko.  Jijjiirama qabatamaa hawwii bira darbee gochuuf waadaa galuun yeroo kamiyyuu caalaa…

ውፍረትን ስናክም ከመጠነ ክብደት ባሻገር እናስብ

ውፍረትን ስናክም ከመጠነ ክብደት ባሻገር እናስብ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ 1 ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ከመጠን ያለፈ ውፍረት (obesity) ተጠቂዎች ቢሆኑም ውፍረት እስካሁን በጥናቶች፣ በማኅበራዊ ግንዛቤ እና በህክምናው ዘርፍ አሁንም ግልጽ የሆነ ‘መለኪያ (diagnostic tool)’ የለውም። ይህ ግልጽ ያለ መመርመሪያና ግንዛቤ እጥረት ትክክለኛ ምርመራና ህክምና እንዳይደረግለት እንቅፋት ሆኗል። የውፍረት ህክምናዎች ብዙውን ጊዜ የሚያተኩሩት ውፍረትን ከምንጩ ከመፍታት…

Scroll to Top